Ethiopian SMME Market Place

Ethiopian SMME Market Place This is a place where Ethiopian Small and Medium Manufacturing Enterprises Products are Entertained Government Research Center

05/06/2026
03/06/2026
28/05/2026

እይታ ፫ - የታሪክ አዙሪት
የአፄ ቴዎድሮስ እልህ፣ ራዕይና የቴክኖሎጂ ሽግግር ፍለጋ!

“የቴዎድሮስ ዕዳ - አንዲት ኢትዮጵያ” በተሰኘው (በፊሊፕ ማርስዲን ተፅፎ በብሩክ መኮንን በተረጎመው) ድንቅ መፅሐፍ ላይ አንድ እጅግ አስተማሪ ታሪክ እናገኛለን።
አፄ ቴዎድሮስ በ1847 ዓ.ም (እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1855) ንጉሠ ነገሥት ሆነው እንደነገሡ ካስተላለፏቸው የመጀመሪያ ደብዳቤዎች አንዱ፣ በኢየሩሳሌም ለአንግሊካን ቤተክርስቲያን ሊቀ-ጳጳስ ለሳሙኤል ጎባት የጻፉት ነበር። ጎባት ከሃያ ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ በሚሲዮናዊነት በነበረበት ወቅት ሀገሪቱ በዘመነ መሳፍንት ጦርነትና አለመረጋጋት ስትታመስ በቅርብ ያየ ሰው ነበር።
ንጉሡ ለዚህ ሰው የጻፉት ደብዳቤ የነበራቸውን የዘመናዊነትና የኢንዱስትሪ ራዕይ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የጠየቁት ቄሶችን ሳይሆን የእደ-ጥበብና የቴክኖሎጂ ባለሙያዎችን ነበር!
በደብዳቤያቸውም እንዲህ አሉት፡-
"የሀገራችንን ተጨባጭ ሁኔታ ታውቀዋለህ፣ ምክንያቱም ኖረህበታልና። ሀገራችን የተከፋፈለች፣ አንዱ በአንዱ ላይ የተነሳበት፣ የተበታተነች ሀገር ናት። አሁን ግን እኔ በእግዚአብሔር ኃይል አንድ አድርጌያታለሁ። አሁን ሃይማኖትን የሚሰብክ ቄስ አይደለም እንድትልክልኝ የምፈልገው፤ ሠራተኞችን—በእሳት ሰረገላ የሚሠራ፣ ማረሻ የሚያመርቱትን ነው። ለመሣሪያ መሥሪያ የሚሆነውን ዕቃ ይዘው ወደ እኔ እንዲመጡልኝ አድርግልኝ። እንዲህ ዓይነት ሥራ የሚሠሩ ሰዎች አሉ ሲባል ስለምሰማ ነውና ላከልኝ።"
ቴዎድሮስ ሀገርን አንድ የማድረግን ያህል፣ ያቺን አንድ የሆነች ሀገር በቴክኖሎጂና በሥራ ማዘመን ቀዳሚው ተግባራቸው እንደነበር ከዚህ መረዳት ይቻላል።
በሌላኛው የመፅሐፉ ክፍል ደግሞ ንጉሡ ለቴዎፍሎስ ዋልድሚየር የሥራ ባህላችንን በተመለከተ የነገሩትና ዛሬም ድረስ ሁላችንንም ሊሞግተን የሚገባ እውነተኛ ምልከታ ሰፍሮ ይገኛል፡-
"የእኔ ሀገር ገነት ናት፤ ነገር ግን የምንኖርባት ሁላችንም አ**ች በመሆናችን አዝናለሁ" በማለት ሕዝቡ የሥራ ባህሉን እንዲያሻሽልና እንዲማር ይመክሩት እንደነበር ዋልድሚየር ያስታውሳል።
የዛሬው መልዕክት፡ ሀገርን በዕውቀት፣ በቴክኖሎጂና በጠንካራ የሥራ ባህል መገንባት የትናንትም የዛሬም የቤት ሥራችን ነው!

አዲሱ የኢትዮጵያ ንግድ ፖሊሲ፤ ለማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች የሚከፍተው አዲስ ዕድልኢትዮጵያ በቅርብ ዓመታት ኢኮኖሚዋን ወደ ምርት፣ ወደ ኢንዱስትሪ እና ወደ ውጭ ገበያ ተወዳዳሪነት ለማሸጋ...
27/05/2026

አዲሱ የኢትዮጵያ ንግድ ፖሊሲ፤ ለማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች የሚከፍተው አዲስ ዕድል

ኢትዮጵያ በቅርብ ዓመታት ኢኮኖሚዋን ወደ ምርት፣ ወደ ኢንዱስትሪ እና ወደ ውጭ ገበያ ተወዳዳሪነት ለማሸጋገር በርካታ ማሻሻያዎችን እያከናወነች ትገኛለች። በዚህ ሂደት ውስጥ የተዘጋጀው አዲሱ የኢትዮጵያ ንግድ ፖሊሲ በተለይም ለማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች አዲስ ተስፋና ሰፊ የገበያ ዕድል ይዞ መጥቷል።

ፖሊሲው በዋናነት የሀገሪቱን የንግድ ሥርዓት ዘመናዊ ማድረግ፣ የግል ዘርፉን ተሳትፎ ማጠናከር፣ የውጭ ንግድን ማስፋፋት እና የአምራች ድርጅቶችን ተወዳዳሪነት ማሳደግን ያለመ ነው። ይህም ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ከዚህ ቀደም በነበሩ የአሰራር እና የገበያ እጥረቶች ላይ አዎንታዊ ለውጥ ለማምጣት ይጠቅማል።

አንዱ ዋና ፋይዳ የአምራች ኢንተርፕራይዞች ወደ አገር ውስጥና ወደ ውጭ ገበያ የሚያገኙትን ተደራሽነት ማስፋፋቱ ነው። ፖሊሲው የንግድ ሂደቶችን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ፈቃድ፣ ምዝገባ፣ የጉምሩክ አገልግሎት እና የሎጂስቲክስ ሥርዓት ቀላልና ፈጣን እንዲሆን ያበረታታል። ይህ በተለይ ጥሬ እቃ በማስገባትና ምርት ወደ ውጭ በመላክ ሂደት የሚፈጠሩ መዘግየቶችን ለመቀነስ ይረዳል።

አዲሱ ፖሊሲ የኢትዮጵያን ምርቶች በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ ለማድረግ ትኩረት ይሰጣል። በዚህም አምራቾች የጥራት ደረጃዎችን እንዲያሟሉ፣ የማሸጊያ ሥርዓታቸውን እንዲያሻሽሉ እና የውጭ ገበያ መስፈርቶችን እንዲያሟሉ ድጋፍ ይደረጋል። ይህም የቆዳ ውጤቶች፣ ጨርቃጨርቅ፣ የምግብ ፕሮሰሲንግ እና የብረታ ብረት ምርቶችን ጨምሮ ለብዙ ዘርፎች የውጭ ገቢ ምንጭ ለመፍጠር ያግዛል።

ፖሊሲው በተለይ አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞችን ወደ መደበኛ የንግድ ሥርዓት ለማምጣት ያተኮረ ነው። የፋይናንስ ተደራሽነት፣ የንግድ መረጃ አቅርቦት፣ የኢ-ኮሜርስ አገልግሎት እና የችሎታ ማጎልበቻ ስልጠናዎች በማስፋፋት እነዚህ ድርጅቶች ከአገር ውስጥ ገበያ ባሻገር ክልላዊና ዓለም አቀፍ ገበያዎችን እንዲደርሱ ያግዛል።

ማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ በብዙ ሰዎች ላይ የሥራ ዕድል የሚፈጥር በመሆኑ የንግድ ፖሊሲው ተግባራዊ መሆን በሀገሪቱ የሥራ እድል ፈጠራ ላይ ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል። አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ሲስፋፉ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የክህሎት ልማት እና የምርት ጥራት መሻሻል ይከተላል። ይህም የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ከጥሬ እቃ ላኪነት ወደ እሴት ጨማሪ ኢንዱስትሪ እንድትሸጋገር ያግዛል።

አዲሱ የኢትዮጵያ ንግድ ፖሊሲ ለማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች ከቀድሞው የተሻለ የንግድ ምህዳር ለመፍጠር የሚያስችል መሆኑ እየታየ ነው። የገበያ ተደራሽነት፣ የውጭ ንግድ ዕድል፣ የቴክኖሎጂ ድጋፍ እና የአምራች ድርጅቶች ተወዳዳሪነት መጠናከር ፖሊሲው የሚያመጣቸው ዋና ፋይዳዎች ናቸው። እንደ ሀገርም ይህን ፖሊሲ በተግባር ማዋል ከተቻለ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የኢንዱስትሪ እና የንግድ ማዕከል ለመሆን ያላትን ዕድል የበለጠ ማጠናከር ትችላለች።

27/05/2026

እይታ ፩
======
*የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ፡ ለኢትዮጵያ ብልጽግና ቁልፍ፣ ከታሪካችን የምንማረው ትልቅ ትምህርት!*

ኢትዮጵያ ወደ ዘላቂ እድገትና ወደ የተሻለ የኑሮ ደረጃ ለመድረስ ከምትመርጣቸው የኢኮኖሚ መንገዶች መካከል የአምራች ኢንዱስትሪ (Manufacturing Industry) ዘርፍ ቀዳሚ ስፍራ ይይዛል። የአምራች ኢንዱስትሪው የሀገር ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ብቻ ሳይሆን፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የፈጠራ እድገትና የሥራ ዕድል መፍጠሪያ ዋና መሠረት ነው።

ሆኖም፣ ወደፊት ለመጓዝ ከመፈለጋችን በፊት “ለምን እስካሁን የኢንዱስትሪ ሽግግር ማድረግ አልቻልንም?” የሚለውን ታሪካዊ ጥያቄ በጥልቀት መመልከት ያስፈልጋል።

አምራች ኢንዱስትሪ ለምን አስፈላጊ ሆነ ?

የአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ለአንድ ሀገር ብልጽግና እና ሉዓላዊነት ወሳኝ የሚሆንባቸው በርካታ ምክንያቶች አሉ። ከእነዚህ መካከል፦

1. ለዜጎች የሚፈጥረው የሥራ ዕድል
አምራች ኢንዱስትሪዎች በሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል ይፈጥራሉ። በተለይ የወጣቶች እና የሴቶችን የሥራ አጥነት ለመቀነስ እና ስራ ፈጣሪ እንዲሆኑ በማድረግ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ ትልቅ ሚና አላቸው።

2. የውጭ ምንዛሬ ግኝት
በሀገር ውስጥ የሚመረቱ ምርቶች ወደ ውጭ ገበያ ሲላኩ ለሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ያስገኛሉ። ይህም የኢኮኖሚ አቅምን ያሳድጋል።

3. የቴክኖሎጂ እና ፈጠራ እድገት
ኢንዱስትሪ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ጋር ተያይዞ ስለሚሄድ፣ የፈጠራ ባህልን ያበረታታል። የምርምርና ልማት (Research & Development) ሥራዎችም እንዲስፋፉ ያደርጋል።

4. ከውጭ ጥገኝነት መውጣት
ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በማምረት መተካት ሲቻል፣ ሀገራችን በውጭ ገበያ ላይ ያላትን ጥገኝነት በመቀነስ ሉዓላዊነታችንን ማረጋገጥ ያስችላል፡፡

*የታሪካችን ትልቅ ስህተት፡ የእደ-ጥበብ ባለሙያዎችን ማግለል*
ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ የብረት ሥራ፣ የሸክላ ሥራ፣ የቆዳ ሥራ እና የሽመና ጥበብ ያላት ሀገር ነበረች። እነዚህ ሙያዎች በእውነቱ የኢንዱስትሪ መሠረቶች ነበሩ።

ነገር ግን ማህበረሰባችን ለእነዚህ ባለሙያዎች የነበረው አመለካከት የኢንዱስትሪ እድገታችንን ገድቦታል።

*1. የንቀት ባህል*
ብረት አቅላጮች፣ ሸክላ ሠሪዎች፣ ቆዳ ፋቂዎች እና ሌሎች የእደ-ጥበብ ባለሙያዎች ክብር ከማግኘት ይልቅ ሲገለሉና በዝቅተኛ እይታ ሲታዩ ኖረዋል። ይህም ሙያውን እንደ ዝቅተኛ ሥራ እንዲቆጠር አድርጎታል።

*2. የእውቀት ሽግግር መቋረጥ*
ባለሙያዎቹ ያላቸውን ጥበብ በምስጢር እንዲይዙና ለልጆቻቸው ብቻ እንዲያስተላልፉ በማህበራዊ ጫና ተገደዋል። በዚህም ምክንያት እውቀቱ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተሻሻለ እንዳይሄድ ገድቦታል።

*3. የኢንዱስትሪ አብዮትን ማጣት*
አውሮፓውያን የእጅ ጥበብ ባለሙያዎቻቸውን ከሳይንስ ጋር በማገናኘት ወደ ዘመናዊ ኢንዱስትሪ ሲሸጋገሩ፣ እኛ ግን የፈጠራ አቅም ያላቸውን ሰዎች በማግለላችን የኢንዱስትሪ መሠረታችንን ማጠናከር አልቻልንም።

“አንድ ማህበረሰብ ጥበበኛ እጆችን በናቀ ጊዜ፣ በባዕድ ምርቶች ተገዥ መሆኑ አይቀሬ ነው።”
ከታሪካችን ተምረን ዛሬ ምን ማድረግ አለብን?

ዛሬ የተጀመሩ እንደ "*ኢትዮጵያ ታምርት”* ያሉ ንቅናቄዎች ታሪካዊ ስህተታችንን ለማረም ጥሩ እድል ናቸው። ይህን ለማሳካት ግን የሚከተሉት ተግባራዊ እርምጃዎች ያስፈልጉናል።

*1. ለሙያ ክብር መስጠት*
የቴክኒክና ሙያ ስልጠናዎችን (TVETs) እንደ ዝቅተኛ አማራጭ ማየትን ማቆም አለብን። በዚህ ደረጃ የሚሰጡ ትምህርቶች የኢኮኖሚው ሞተር መሆናቸውን በግልጽ መገንዘብ ያስፈልጋል።

*2. ጥበብን ከሳይንስ ጋር ማገናኘት*
ባህላዊ የእደ-ጥበብ ስራዎቻችንን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በማገዝ ወደ አምራች ኢንዱስትሪ ደረጃ ማሳደግ ይገባል።

*3. የሀገር ውስጥ ምርትን ማበረታታት*
የሀገራችንን ምርቶች መጠቀምን ባህል ማድረግ አለብን። የሀገር ውስጥ አምራቾችን መደገፍ የኢኮኖሚ ነፃነት መሠረት ነው።

*የዛሬው እውነታ*
ይህን ጽሑፍ ለመጻፍ መነሻ የሆነኝ፣ ሰሞኑን በአንድ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ ከቀጨኔ መድኃኒዓለም አካባቢ የሸክላ ሥራ ከሚሰሩ ቤተሰቦች የተገኘች አንዲት ታዳጊ ድምፃዊት ስለ ሙያውና ስለ ሙያተኞቹ በማህበረሰቡ ውስጥ ያለውን አመለካከት በግልጽ መናገሯ ነው።

ይህ አሁንም ድረስ በማህበረሰባችን ውስጥ ለሙያና ለእደ-ጥበብ ያለው አመለካከት ምን ያህል ለውይይትና የቀጣይ ስራችን ትኩረት እንደሚያስፈልገው ትልቅ ማሳያ ነው።

*እንደ ማጠቃለያ*
ኢትዮጵያዊያን ያለንን የተፈጥሮ ሀብትና የሰው ኃይል በአግባቡ ተጠቅመን ወደ አምራችነት ካልተሸጋገርን፣ የጀመርነው የብልጽግና ጉዞ የታለመለትን ትልም ላያሳካ ይችላል፡፡

ትናንት ያገለልናቸውን ጥበበኞች ዛሬ በክብር፣ በእውቀትና በቴክኖሎጂ ማበረታታት አለብን። የኢንዱስትሪ እድገት የሚጀምረው ጥበበኛ እጆችን በማክበር ነውና።


#ኢንዱስትሪ
#እደጥበብ
#ለኢኮኖሚ
#ዕድገት

17/02/2026
የአፍሪካን የብልፅግና ታሪክ የሚያበስረው ታላቁ ነፃ የንግድ ቀጣና *********************** አፍሪካ የኢኮኖሚ ድንበሮቿን በመስበር በአንድ ግዙፍ የጋራ ገበያ ጥላ ሥር ለመሰባሰብ ...
15/02/2026

የአፍሪካን የብልፅግና ታሪክ የሚያበስረው ታላቁ ነፃ የንግድ ቀጣና
***********************

አፍሪካ የኢኮኖሚ ድንበሮቿን በመስበር በአንድ ግዙፍ የጋራ ገበያ ጥላ ሥር ለመሰባሰብ የጀመረችው ታሪካዊ ጉዞ አዲስ ምዕራፍ ላይ ደርሷል።

በአውሮፓውያኑ 2021 ሥራ የጀመረው የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና (AfCFTA)፣ የአህጉሪቱን ሸቀጦች እና አገልግሎቶች በማስተሳሰር የኢኮኖሚ ውህደትን ለማረጋገጥ የተወጠነ ታላቅ ተስፋ ሆኖ ነው።

ይህ ስምምነት የታሪፍ መሰናክሎችን በማንሣት እና የንግድ ፍሰትን በማፋጠን፣ አህጉሪቱን ወደ ኢንደስትሪ መር ኢኮኖሚ እና ዘላቂ ልማት የማሸጋገር ግዙፍ የቤት ሥራን አንግቧል።

ከኤርትራ በስተቀር 53 የአፍሪካ ኅብረት አባል ሀገራትን ያቀፈው ይህ ቀጣና፣ በሀገራት ብዛት ከዓለም ትልቁ የንግድ መድረክ ሆኖ ተመዝግቧል።

የዓለም ባንክ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት፣ ስምምነቱ ሙሉ በሙሉ ሲተገበር በአውሮፓውያኑ 2035 የአህጉሪቱን ገቢ በ450 ቢሊዮን ዶላር የማሳደግ አቅም አለው።

ከ1.4 ቢሊዮን በላይ ሕዝብ የሚገኝበትን ይህን ሰፊ ገበያ በማስተሳሰርም፣ አህጉር በቀል የንግድ ልውውጥን በ81 በመቶ ያሳድገዋል ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንትን (FDI) እስከ 111 በመቶ በማሳደግ የመሠረተ ልማት እና የኢንዱስትሪ ተደራሽነትን ያፋጥናል።

የመጀመሪያው የሸቀጦች ንግድ በጥር 2021 ቢጀመርም፣ ትግበራው አሁንም የታሪፍ ቅነሳ ፍጥነት ማነስ፣ የሰዎች ነፃ እንቅስቃሴ (ቪዛ) ውስንነት እና የሎጂስቲክስ መሰናክሎች እየገጠሙት ይገኛል።

ይሁን እንጂ ስምምነቱ ከንግድ ባለፈ የሥራ ዕድል ለመፍጠር፣ የሴቶችን እና የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ቁልፍ ሚና አለው።

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስኬት በሀገራቱ ቁርጠኝነት ላይ የሚወሰን ሲሆን፣ ይህም ለአህጉሪቱ "አጀንዳ 2063" ስኬት ዋነኛው መሠረት ነው።

13/02/2026

ለማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች ታላቅ ዕድል!
======///======
የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪው ቤተሰብ መሰባሰቢያ፣ ሀገራዊ አቅማችንን የምናሳይበት ታላቅ መድረክ — “ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2018” እየተዘጋጀ ነው!

📅 ሚያዝያ 24 – 28 / 2018 ዓ.ም
📍 በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል

ለምን ይሳተፉ?

👉ምርቶዎትን ለአገር ውስጥና ለአለም አቀፍ ገዢዎች ያቀርቡ

👉አዳዲስ የገበያ እድሎች ያግኙ

👉ከኢንቨስተሮችና ከኢንዱስትሪ ባለሙያዎች ጋር ይገናኙ

👉የኢትዮጵያ የማምረት አቅምን በአለም አቀፍ ደረጃ ያሳዩ

👉ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን ፊት ለፊት በአካል በማግኘት የሚፈልጉትን ጥያቄ ያቀርቡ

ኢንተርፕራይዝዎን ያስተዋውቁ፤ ንግድዎን ያሳድጉ፤ የኢትዮጵያን ምርት አብረን እናሳይ!

ለመሳተፍ እና ለተጨማሪ መረጃ፦

📞 +251 911 936544
📞 +251 938 938531
📞 +251 921 042680

!



https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment

https://forms.gle/4od8gAw2Pfdmuhe97
13/02/2026

https://forms.gle/4od8gAw2Pfdmuhe97

Hello! Thank you for expressing interest in the Africa Continent Free Trade Area (AfCFTA) Digital Inclusion and Entrepreneurship Programme (ADIEP) powered by Google Hustle Academy. To ensure the half day training is the best option for your business, we have put together this short survey. It should...

06/02/2026

The Google Hustle Academy, through the AfCFTA Digital Inclusion & Entrepreneurship Programme (ADIEP), delivers a bootcamp-style professional education for African SME intensive, short-term, and highly practical training designed to rapidly build digital, entrepreneurial, and trade-related skills. It targets 7,500 small and medium enterprises across Africa, including Ethiopia, to prepare them for success in the digital economy and AfCFTA trade environment.

What “Bootcamp Style” Means in ADIEP

- Immersive & Intensive: Sessions are condensed into a few weeks, with structured modules covering business strategy, digital marketing, financial planning, and trade readiness.
- Hands-On Learning: Participants work on real business challenges, applying tools like Google Ads, analytics, and cloud solutions directly to their enterprises.
- Collaborative Environment: SMEs learn in cohorts, sharing experiences and building networks across African markets.
- Outcome-Oriented: The focus is on measurable growth—improved digital presence, readiness for cross-border trade, and stronger entrepreneurial capacity.

Key Features of ADIEP

- Target Audience: Young African entrepreneurs and SMEs seeking to expand digitally and leverage AfCFTA opportunities.
- Scale: 7,500 SMEs will be trained across Africa.

- Skills Covered:

- Digital marketing & e-commerce strategies.
- Financial management and investment readiness.
- AI adoption and cloud-readiness for SMEs.
- Trade facilitation under AfCFTA frameworks.

- Cost: Free of charge, sponsored by Google Hustle Academy.

- Goal: Empower SMEs to thrive in the digital economy and participate competitively in continental trade.

Address

Rwanda
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:00
Tuesday 08:00 - 17:00
Wednesday 08:00 - 17:00
Thursday 08:00 - 17:00
Friday 08:00 - 17:00

Telephone

+251913902568

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian SMME Market Place posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethiopian SMME Market Place:

Share

Category