Ye Weldu ljoch

Ye Weldu ljoch Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ye Weldu ljoch, Family style restaurant, Addis Ababa.

25/07/2022

+ አበረታች መድኃኒት +

የአበረታች መድኃኒት ጉዳይ የአትሌቲክሱን ዓለም ሲያምሰው የሚኖር ጉዳይ ነው፡፡ በስፖርታዊ ጨዋታዎች ላይ የአሸናፊነት ሜዳሊያ አጥልቀው ፈንጠዘው የሀገራቸውን ሰው ያስፈነጠዙ አትሌቶች ‹ጉድና ጅራታቸው› ከወደኋላ መጥቶ ያስመዘገቡትን ድል እየተቀሙ ፣ ሐፍረት ሲከናነቡ ይታያል፡፡ ለዚህም ምክንያቱ ማሸነፍ የቻሉት በድካማቸው ብቻ ሳይሆን ‹በሚወስዱት መድኃኒት› ሆኖ በመገኘቱና ኃይል ሰጪ መድኃኒት ወስደው ከሰው ጋር የማይመጣጠን ጉልበት ጨምረው በመግባታቸው ነው፡፡

ይህንን ዜና ስንሰማ ብዙዎቻችን አንዲት ኢትዮጵያዊት ጀግና አትሌት ትዝ ሳትለን አልቀረችም፡፡ ይህች አትሌት የለንደን ኦሎምፒክ የ5000 ሜትር የሴቶች የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊዋ ጀግናዋ አትሌት መሠረት ደፋር ናት፡፡ መሠረት ደፋር አበረታች መድኃኒት በመውሰድ ብቻ ሳይሆን አበረታች መድኃኒቷን እዚያው የመሮጫ ትራኩ ላይ አውጥታ ያሳየችና ወደ ካሜራ ቀረብ አድርጋ ለዓለም ‹አበረታች መድኃኒቴ ይኼ ነው!› ብላ ያሳየች ጀግና ናት - እውነትም መሠረት ደፋር!

ከራሴ ልጀምር፡፡ የ2012ቱ የለንደን ኦሎምፒክ በተካሔደበት ወቅት የነበርሁት ከፍተኛ ሙቀት ካለበት በመካከለኛው ምሥራቅ በተባበሩት የአረብ ኢመሬትስ የአቡዳቢ ከተማ ነበር፡፡ ሙቀቱም ማቀዝቀዣውም የሚመች ባለመሆኑ የአየሩ ሁኔታ አድካሚና ተኝተው ሲነቁ ዳግመኛ መተኛት የሚያሰኝ ዓይነት ነበር፡፡ በሌሊት የሚተላለፈውን የነመሠረትን የሩጫ ውድድር እንድመለከት አብረውኝ የነበሩት ሰዎች ሲቀሰቅሱኝም ከአልጋ የተነሣሁት በብስጭትና በይሉኝታ ሩጫው ከተጋመሰ በኋላ ነበር፡፡ የሩጫው የመጨረሻ ሰዓት ላይ መሠረት አስደናቂውን ድል አስመዘገበች፡፡ እንደ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እኛም በደስታ አጨበጨብን፡፡

ከዚህ በኋላ መሠረት ባንዲራ ለብሳ ስትሮጥ ለማየት ስንጠባበቅ አንዳች ነገር ከደረቷ አውጥታ ተንበረከከች፡፡ ከደረቷ ባወጣችው ጨርቅ መሰል ነገር ፊቷን ሸፍና አቀርቅራ ታለቅስ ጀመር፡፡ ቀና ስትል ግን በፊቷ ላይ የለጠፈችው ድንግል ማርያምን ከተወደደ ልጇ ጋር የሚያሳይ ሥዕል ነበር፡፡ የሁላችንም ዕንባ ሳናስበው ከዓይናችን ወረደ፡፡

መሠረት ሥዕሉን ከፊቷ ላይ አንሥታ ከተንበረከከችበት ተነሣች፡፡ የእመቤታችንን ሥዕልም ወደላይ ከፍ አድርጋ አሳየች ፤ ወደ ካሜራውም አቀረበችው ፤ ኦሎምፒክን ለሚመለከተው የዓለም ሕዝብ መሠረት ሥዕለ ማርያምን አሳለመችው፡፡ እመቤታችንን የሚወዱ በትኩስ ዕንባ ፤ እርስዋን የሚጠሉ ደግሞ በንዴት ተቃጠሉ፡፡ መሠረት ያቀፈቻትን ድንግል ማየት ባይወዱ እንኳን ድንግል ያቀፈችውን ጌታ ማየት ቢችሉ ምን ነበረበት?

ይህን ካየሁ በኋላ እኔም እንቅልፌ ጠፋ ፤ ከየአቅጣጫው ስለ መሠረት የሚባለውን ስፈላልግ ነጋ፡፡

ጨዋታውን የሚያስተላልፉት ኮሜንታተሮች ምን እንደሚሉ ግራ ተጋቡ፡፡ ልክ የእመቤታችንን ሥዕል ሲታይ እንዲህ ተባብለው ነበር ፡-

ኮሜንታተር 1 - ተመልከት ... አአአህ! (ሥዕሉ ቀርቦ ሲታይ) ያው እንደሚታወቀው በአንዳንድ ቦታዎች ይኼ ነገር መልእክት ይኖረዋል ፤ አይደል እንዴ?
ኮሜንታተር 2 - አዎ በኢትዮጵያ ጠንካራ የክርስቲያን ማኅበረሰብ አለ ...
ኮሜንታተር 1 - አዎ .. አዎ ... እናም እንደሚመስለኝ እእ... የምንመለከተው ነገር ...... እእእ.... አሥራ አምስት ፣ ዜሮ አራት ከሃያ አምስት ... መሠረት ደፋር!! ብሎ አቆመ፡፡ መሠረት እኛን ብቻ ሳይሆን ኮሜንታተሩንም የሚናገረውን አሳጣችው፡፡ የሩጫውን አደባባይ ዐውደ ምሕረት አድርጋበት የማያውቀውን ጉባኤ መምራት ከየት ያምጣው?

ወዲያውኑ የዜና አውታሮችና በዓለም ዙሪያ ያሉ ድንግል ማርያምን የሚወዱ ክርስቲያኖች ስለመሠረት ደፋር የተሰማቸውን ለመግለጽ ተሽቀዳደሙ፡፡

አሶሺየትድ ፕሬስ መሠረት ያሳያችውን ሥዕለ ማርያም ‹ፎቶ› ብሎ ብቻ ሊያድበሰብሰው ሲሞክር ሮይተርስ ግን ‹ሃይማኖታዊ ሥዕል ያለበት ከጨርቅ የተሠራ..› ብሎ ገልጾታል፡፡ የዜናው አዘጋገብ ያልተመቻቸው ብዙ ክርስቲያኖች በተለይ አሶሺየትድ ፕሬስ ላይ ትችታቸውን አዝንመዋል፡፡ በአንጻሩ ሃይማኖታዊ ሚድያዎች ደስታቸውን የሚገልጽ ዘገባ ይዘው ቀረቡ፡፡ የካቶሊክ ዜና አገልግሎት (CNA) ‹ድንግል ማርያም ከኦሎምፒክ ወርቅ አሸናፊዋ ጋር የመጨረሻውን መስመር አብራ ተሻገረች!› ሲል ዘገባውን አወጣ፡፡ ኤክዛማይነር ዶት ኮም የተሰኘው ድረ ገጽ ደግሞ ‹‹ድንግል ማርያምና ሕጻኑ ክርስቶስ በኦሎምፒክ አምስት ሺህ ሜትር ውድድር ላይ (ታዩ)!›› ብሎ አወጣ፡፡ በማኅበራዊ ሚድያም ብዙዎች ደስታቸውን ገለጹ፡፡ ኢትዮጵያውያን ፣ ግብፃውያን ፣ ላቲን አሜሪካዊያን ፣ ስፔናዊያን ሌሎችም በማኅበራዊ ሚድያ የመሠረትን ምስክርነት እንዲህ አደነቁ፡፡

‹ዕንባዬን ማቆም አልቻልኩም!›

‹ኢትዮጵያውያን የተባረኩ ናቸው ፤ ቅዱሱ ጽዋ እነርሱ ጋር እንደሆነ አንብቤያለሁ!›

‹መሠረት ደፋር እንኳን ደስ አለሽ ፤ ክርስትናችንን ስለመሰከርሽልን እናመሰግናለን!›

‹ማታ ስመለከተው ከዓይኔ ዕንባ ፈለቀ ፤ ያየሁት NBC ላይ ነበር ፤ ካሜራው ግን ለምን ቶሎ ወደ ሌላ ቦታ አዞረው?›

‹ኮሜንታተሮቹን አልወደድኳቸውም ፣ ምን ያህል ስሜት የሚነካ ቅጽበት እንደነበር አልገባቸውም›

‹የዐሥራ አምስት ዓመት ልጄ አገር አቋራጭ (XC) እና የትራክ ውድድር ትሮጣለች፡፡መሠረትን ስታይ ‹ኦ! ከዚህ በኋላ የቅድስት እናታችንን ሥዕል ይዤ መሮጥ መጀመር አለብኝ› አለች!›

የመሠረት ምስክርነት በማኅበራዊ ሚድያ ብቻ ሳይወሰን ወደ ቤተ መቅደስም ገብቶ የስብከት ርዕስ ሆነ፡፡ እርስዋ አርብ ለቅዳሜ አሸንፋ ያሳየችውን ነገር እሑድ የሰንበት ቅዳሴ ከተቀደሰ በኋላ አቡነ ቄርሎስ ጊዮርጊስ የተባሉ ግብጻዊ አባት በሎስ አንጀለስ በሚገኘው የቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን አስተማሩበት፡፡

‹‹ከእናንተ መካከል ትናንት የኦሎምፒክ ጨዋታ ያየ ማን ነው? በአምስት ሺህ ሜትር ሴቶች ያሸነፈችውን ኢትዮጵያዊት ወጣት አላያችኋትም? መጀመሪያ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ሆና ነበር የሮጠችው፡፡ ውድድሩ ሊያልቅ ጥቂት ሰከንዶች ሲቀሩት ግን አንደኛ ሆነች፡፡ ሩጫውን ስትጨርስ ተንበረከከች... በነገራችን ላይ የምነግራችሁ ዓለም ሁሉ ስለሚመለከተው ኦሎምፒክ ነው ... ከደረትዋ የሆነ ነገር ለማውጣት ታገለች ... አወጣችው ... ምን እንዳወጣች ታውቃላችሁ? ... የድንግል ማርያምን ሥዕል! ... ኢትዮጵያዊት ስለሆነች ያወጣችው ሥዕል በእኛ ቤተ ክርስቲያን እንዳለው ዓይነት ሥዕለ ማርያም ነበር .. ወደ ካሜራው አስጠጋችው .. በጣም ደስ ብሏታል ... አምስት ሺህ ሜትር አሸንፋ ነው እንግዲህ ... ስሟም ደፋር ይባላል ... ስታሸንፍ ግን ቅድስት ማርያምን አሳየች ... አያችሁ ድንግል ማርያም እኮ ትወደዳለች!›

አዎ በዚያች ምሽት መሠረት የብዙኃንን ልብ በደስታ ሞልታው ነበር፡፡ የባሕርያችንን መመኪያ ወላዲተ አምላክን በዓለም አደባባይ ስታሳየን ልባችን በደስታ ተሞላ .. አንድ ወዳጄ ይህን ነገረኝ ‹‹ሆስፒታል ስለምሠራ የዚያን ዕለት አዳሪ ነበርሁ ... የሆስፒታሉ ሠራተኞች እና ሕሙማን ውድድሩን ይመለከቱ ነበር ... መሠረት ስታሸንፍ ሁሉም በአንድነት ጮኸ ተደሰተ ... ጥቂት ቆይቶ የእመቤታችንን ሥዕል ሲታይ ግን የታመሙት ሳይቀሩ ከአልጋቸው እየተነሡ ፈነደቁ ... መሬት ሳሙ...››

በዚያች ምሽት የእመቤታችን ወዳጅ ሆኖ መሠረትን ‹ዕድሜ ይስጥሽ ፣ እመብርሃን ትባርክሽ!› ያላላት ሰው አልነበረም፡፡ በዚያች ምሽት የማይዘነጋ ፣ ከልብ የማይወጣ ትልቅ ስብከት ተሰበከ!

መ/ር አቡኑ ማሞ የተባሉ ካህን በዚያች ዕለት በገጠሙት ግጥማቸው እንዳሉት በእርግጥም ‹ለንደን ግሸን ሆነች!›... እርሳቸው ልብ የሚነካ ግጥማቸው ይህን ጽሑፍ ያሳርጉልናል :-

የእሳት ትንታግ ፍንጣሪ
የድል ዜማ ወገን አኩሪ

የክብር ጥግ ማማ
የደስታ ውበት ቄጤማ

የመስቀሉን ኃይል ከግሸን የጠበሉን በረከት ዘግና
ይኸው አየኋት በለንደን የእሳት ልጅ እሳት ሆና

የደም አዙሪት ምሬቱ
የእሳት ትግል ሽረቱ

እየፈላባት ሐሞቷ እየታገላት ሲቃ
ታቦቷን ከራሷ ሳይሆን ከደረቷ ላይ ደብቃ
ተሻገረችው ያንን ጉድ አስለቀሰችን ነፍርቃ

ጀመረች አግዥኝ ብላ
ድንግልን በደረቷ አዝላ

ታሪክ ናት ይህች ማርያም ለተማጸናት በብርቱ
ልጇን ላመነ በልቡ ፍቅሯን ላሰረ በአንገቱ

ረሳችውና ድካሟን የልፋት ውጤት ወርቋን
ከፍ አደረገች በሥዕሏ የድንግል ማርያምን ስሟን

ግሸን ሆነች አሉ ለንደን ተቀይራ
መሠረተ ሕይወት ድንግል ተዘምራ

እምነት ከጉያ ውስጥ ድንገት ፈለቀና
ሃሌ ሃሌ ሆነ ድካም ተረሳና

የእኛ ርግብ አማኝቷ
የኢትዮጵያ ልጅ መሠረቷ
ቢላላባት ያሰረችው ቢበጣጠስ መቀነቷ
ተወራርዳ አሸነፈች በጌታ እናት በአዛኚቷ


ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ለመጋቢት16 ዝክር የተጻፈ
2008 ዓ.ም
አዲስ አበባ

16/05/2022

♥♥ #እናቴ #እኔ #ልውለድሽ!♥♥

🔹🔹🔹🔹🔹 🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹

♥♥ ማርገዝ ለሴት ልጅ የተፈጥሮ ስጦታዋ ነው ግን እንዴት አድርጌ እንደማረግዝሽ ባላውቅም፤ እናቴ ልወልድሽ አስቤያለው። ስቃይሽ አልገባኝ ቢል መስዋትነትሽን ባልረዳው፤ ውለታሽን መክፈል ቢያቅተኝ፤ ጥልቅ የሆነው እናትነትሽን ለመመርመር ቢከብደኝ፤ በተራዬ ልወልድሽ ወሰንኩኝ። ምን ላድርግ ፍቅርሽን እኮ የሰው ህሊና ሊመረምረው ፤ ውለታሽን የሰው ልብ ሊሸከመው አይችልም። እንኳን ሰው እኔ የስጋሽ ክፋይ አልተረዳሁትም.......እናም ልወልድሽ ወሰንኩኝ!

♥♥ አየሽ ምጥሽን መረዳት ቢሳነኝ፤ ስቃይሽን፤ ውለታሽን፤ መስዋትነትሽን መመዘኑ ቢከብደኝ፤ በተራዬ ልወልድሽ ተመኘው። ከንቱነቴ ነው ይህን ያስመኘኝ......ባለዕዳ መሆኔ ህሊናዬን ዘወትር ስለሚያሳምመው። የፍቅርሽን በተግባርሽ ባየውም፤ ጥልቀቱን መረዳት ግን አልተቻለኝም!
ረቂቅ ሆንሽብኝ፤ እናትነት እንዴት እንዲህ ውስብስብ ሆነ?
"እግዚያብሔር በሁሉም ቦታ ላለመሆን ሲል እናትን ፈጠረ" ይላሉ አበው። እናትነት ትናንሽ ፈጣሪነት ነው። ከፈጣሪ በታች እጅግ ጥልቅ የሆነብኝ ያንቺ ፍቅር ነው። ፈጣሪስ ለሰው ልጅ የከፈለውን መስዋትነት ሁሉ በጥበቡ ቻለው፤ እናቴ አንቺ እንዴት ቻልሽው? ይህ ምሥጢር ግራ ቢገባኝ እኮ ነው፤ ልውለድሽ ያልኩት። ቢያንስ በትንሹ ውለታሽን ለመክፈል እንዲቻለኝ።

♥♥ ሁሉም ሰው በእናቱ ይታበያል....ሁሉም ሰው የራሱን እናት የተለየች እንደሆነች ሆኖ ይመሰክራል፤ ሁሉም የእናቱ ፍቅር የእናቱ መስዋትነት፤ የእናቱ መከራ፤ ከየትኛውም እናት የበለጠ እነደሆነ ይናገራል። ምን እንናድርግ፤ እናትነትን የሚያስረዳ ነገር ብናጣ እኮ ነው። እና እኔም በእናቴ ብታበይ ...ግብዝነቴን አትታዘቡት።እናቴ እንዳልኩሽ እንዴት እንደማረግዝሽ አላውቅም.......ልወልድሽ ግን ወስኛለው። ብለፋ፤ ብጥር፤ አንቺ የደረስሽበት የደግነት ጣሪያ ላይ መድርስ አልተቻለኝም። ከብዙ ማሰብ በኋላ አንድ ድምዳሜ ላይ ደረስኩኝ፤ ምንም አይነት ሰው ብሆን፤ የእናትን ያህል ፍቅር እና ደግነትን እንዲሁም ቻይነትን መጎናጸፍ አይቻልም። በቃ የእናትን ያህል አፍቃሪ ለመሆን እናት መሆን ግድ ይላል። ማንም ተራ የሰው ልጅ ሊችለው አይችልም።!

♥♥ እመኚኝ ፈጣሪ ላንቺ እድሜ ለኔ ብርታቱን ይስጠን እንጂ እወልድሻለው። ሰዎች ይህን ሃሳቤን ሲሰሙ ተሳለቁብኝ። ልጅ እንዴት እናቱን ይወልዳል??? ብለው ተዘባበቱብኝ።
እኔ ግን መላ አላጣም......ስቃይዋ ከንቱ እንዳልቀረ ባሳውቃትስ? ሰው እንደወለደች እንድታውቅ ሰው ሆኜ ባሳያትስ? ህመሟ ልፋትዋ ውሃ እንዳልበላው በስራዬ ብመሰክርላትስ? ደግነቷን ሳልበርዝ በደሜ እንዳቆየሁት ባረጋግጥላትስ? ዳግም ወለድኳት ማለት አይደለም?
እናቴ ኑሪልኝ። በጸጋው ለምልሚልኝ፣ በበረከቱ በደስታው ከፍ ከፍ በይልኝ!

♥♥ መልካም የእናቶች ቀን፤ ምንም እንኳን ለእናት 365 ቀን ባይገደብላትም፣ እያንዳንዷ ቀናት የእሷ ቢሆኑም በድጋሚ መልካም የእናቶች ቀን!! ♥♥

መምህር ዘላለም መንግስቱ

30/03/2022
13/03/2022
02/03/2022

🚹🚺 ሕይወት የሁለት ነገሮች ድምር ውጤት ናት። 🚺🚹

🌀 ማግኘት አለ 👉 ማጣት አለ
🌀 መወለድ አለ 👉 መሞት አለ
🟢 ደስታ አለ 👉 ሀዘን አለ
🟢 እንባ አለ 👉 ሳቅ አለ።

🚻 ሁለቱም የህይወት አካሎች ናቸው። አንዳንዴ ህይወት እንደ ሸማኔ መወርወሪያ የሁለቱንም ጫፍ እያስነካች ትመልሰናለች። አንድ ቀን 24 ሰዓት አለው። 12ቱ ሰዓት ብርሃን 12ቱ ሰዓት ጨለማ ነው። አይ እኔ ጨለማ አልወድምና ለሊቱ ይቅርብኝ ብንል ቀናችን ጎዶሎ ነው ሚሆነው ። አንድ አመትም ክረምትና በጋ አለው። አይ ጭቃ አልወድምና ክረምቱ ይቅርብኝ ብንል አመታችንም ጎዶሎ ነው ሚሆንብን ።

ስለዚህ ህይወትም ያለ ችግር ደስታውን ብቻ እንኑረው ብንል ጎዶሎ ህይወት ነው ምንኖረው። አንዳንዴ ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ችግር ውስጥ የሚከተን ሕይወታችንን ሙሉ ለማድረግ ነው ። ከለሊት በኋላ ንጋት እንጂ ሌላ ሌሊት አይመጣም ። ከመከራ ቡሃላም ደስታ እንጂ ሌላ መከራ አይመጣምና ታገስ።

ወዳጄ አንድ ኮኮብ ዙሪያው በጨለመ ቁጥር እሱ ይበልጥ ይበራል። ህይወትህ የጨለመብህ ይበልጥ እንድታበራ ነውና ተደሰት። እህቴ በተለያየ ሀገር በተለያየ ስራ ውስጥ እራስሽን ለመለወጥ በተለያየ አይነት ችግር ውስጥ ተወጥረሽ ይሆናል።

ግን የረገበ የክራር ክር ሙዚቃ ማውጣት አይችልም። አንድ ክራር ሙዚቃ ከማውጣቱ በፊት መጀመሪያ ክሩ በደንብ መወጠር አለበት። ህይወት አንቺንም የወጠረችሽ ሚያምር ማንነትሽን ለማውጣት ነው። ወንድሜ እራስህን ለመለወጥ ስትሞክር ብዙ ነገሮች ቅጥል አርገውህ እርር ብለህ ይሆናል።

ግን አስታውስ አንድ መዓዛው የሚያምር እጣን ይሸተን ዘንድ መጀመሪያ እሳት ውስጥ ገብቶ መቃጠል አለበት። አንተንም ሕይወት ያቃጠለችህ ሚያምር ማንነትህ እንዲወጣ ነውና ተደሰት።

🟣🟣🟣🟣🟣🟣🟣🟣🟣🟣🟣

✳ ✳

"ፀሀይዋን ተመልከታት አታምርም? ጨረቃዋስ ከዋክብቱስ ዛፎቹ ወንዙና ተራራውስ አያምሩም ? ያምራሉ ። እኚ ሁሉ ግን ያልፉሉ አንተ ግን በሞት ከዚህ አለም ብትለይ እንኳን በሰማይ ለዘላለም ትኖራለህ ። ፈጣሪ ፍጥረታትንን ሁሉ በቃሉ በመናገር እና በሀሳብ (በሀልዮ) ሲፈጥር አንተን ግን በእጁ አሽሞንሙኖ ፈጥሮሀል። አንተ ማለት ክርስቶስ እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለው ማንም ሚከፍትልኝ ቢኖር ገብቼ እራቴን ከእርሱ ጋር እበላለው ብሎ የተናገረልህ ።

ፈጣሪ አለምን ከፈጠረበት ጥበብ ይልቅ አለምን ያዳነበት ጥበቡ ይበልጣል ተብሎ የተነገረልህ ዋጋ የከፈለልህ የመንግስቱ ወራሽ ውድ ልጁ ነህ። ምን አልባት ዛሬ በተለያየ ሱስ ተይዘህ ይሆናል ምን አልባት ስራ በማጣት ፍቅረኛ በማጣት ትሰቃይ ይሆናል።

ምን አልባት ቤተሰብህ ወገንህ ተስፉ ቆርጦብህ ይሆናል ። ምን አልባት ሞትህን እየተመኘህ ይሆናል። ግን አይዞህ ፈጣሪ በአንተ የጀመረውን ስራ ሳይጨርስ አትሞትም። Never Give Up በቀላሉ ተስፉ አትቁረጥ ። ተመልከት ሰይጣን ተስፉ የለውም ግን ተስፉ አይቆርጥም ። ሰው ግን ተስፉ አለው ግን ተስፉ ይቆርጣል።

✅ አምፖል ሽቦው ከረገፈ አያበራም ጠርሙስ ይሆናል ። የሰውም የብርሃን ሽቦው ተስፉ ነው ። ሰው ተስፉ ቢቆርጥብህ እራስህም ተስፉ ብትቆርጥ የፈጠረህ በአንተ ላይ ተስፉ አይቆርጥብህምና አይዞህ ። 1 ጠጠር አንስተህ ተራራ ላይ ብትወረውር ተራራው ምንም አይሆንም ጠጠሩ ተንከባሎ እግሩ ስር ይሆናል ።

ያን ጠጠር አንስተህ መስታወት ላይ ብትወረውረው ግን መስታወቱ ይሰባበራል። ጠጠሩን በችግር እንመስለውና ችግር ወዳንተ ሲመጣ እንደ መስታወቱ አትሰባበር እንደ ተራራው በቁጥጥር ስር አውለው ።

✅ የተለኮሰ የክብሪት እንጨት ጭድ ላይ ብትጥለው ይቀጣጠላል ። ውሀ ላይ ብትጥለው ግን ውሀው ያጠፉዋል ። የሚያቃጥሉ ነገሮች በህይወትህ ውስጥ ሲከሰቱ እንደ ጭድ አትቀጣጠል እንደ ውሃው አጥፉቸው ።

✅ በረዶ ፀሀይ ላይ ብታረገው ይቀልጣል የተቦካ ሲሚንቶ* ፀሀይ ላይ ብታረግ ግን ይጠነክራል። እንደ ፀሀይ የከረሩ ችግሮች በህይወትህ ሲያጋጥሙህ እንደ በረዶ አትቅለጥ እንደ ሲሚንቶው ጠንክርባቸው። እህቴ ምን አልባት ለስራ ጉዳይ በተለያየ ሀገር ውስጥ ሆነሽ ይሆናል ያለሽው ።መፈጠርሽ ሴትነትሽም አስጠልቶሽ ይሆናል። ግን ክርስቶስ ወደ አለም ሲመጣ ምድራዊ እናት እንጂ አባት አላስፈለገውም የሴት ልጅ ተብሎ እስኪጠራ ድረስ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ብቻዋን ነው ያሳደገችው።

በኛ ቤተክርስቲያን ህንፃ ቤተክርስቲያኑ ተሰርቶ አለቀ የሚባለው
ጉልላቱ ተሰርቶ ሲያልቅ ነው ። ፈጣሪም ፍጥረትን ሁሉ ፈጥሮ ሲጨርስ አዳምን ፈጠረ በመጨረሻም ከጎኑ ሄዋንን ወይም አንቺን የስነ ፍጥረት ጉልላት አርጎ ፈጠረሽ። ስለዚህ እህቴ ክብርት ፍጥረት ነሽና ደስ ይበልሽ።

ምርጥ መጣጥፎች
ሼርርርር

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ye Weldu ljoch posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share