GG health & Social Tips

GG health & Social Tips Social and Health

21/04/2024
23/12/2023

ድምጽን በመስማት ብቻ ጉንፋንን የሚለየው አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ
በህንድ ተመራማሪዎች የተስራው ቴክኖሎጂ ጉንፋን ይዞኛል በሚል ከቢሮ ለመውጣት የሚደረግ ሙከራን ከንቱ ያደርጋል ተብሏል
ሰው ሰራሽ አስተውሎቱ ወደህክምና ተቋማት በመሄድ የሚባክን ጊዜ እና ገንዘብን እንደሚያስቀርም ነው የተነገረው

የህንድ ተመራማሪዎች ጉንፋን የያዘውን ሰው በድምጹ ብቻ መለየት የሚያስችል የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂን አስተዋወቁ።

የሳርደር ቫልባቢ ብሄራዊ የቴክኖሎጂ ተቋም በ630 ጀርመናውያን ላይ ጥናት አድርጓል።

ከጥናቱ ተሳታፊዎች ውስጥ 110ሩ ጉንፋን ያመማቸው ነበሩ የሚለው የቢዝነስ ኢንሳይደር ዘገባ፥ ድምጽ እና ጉንፋን ያላቸው ትስስር በጥናቱ መዳሰሱን አብራርቷል።
የድምጽ መጎርነን ብቻውን የጉንፋን ምልክት አይደለም የሚሉት የኤሌክትሪክ ኢንጂነር ፓንካጂ ዋርሉል፥ ጉንፋን ሲይዘን የድምጽ መርገብገብና ሌሎች ለውጦች እንዳሉ አብራርተዋል።

የጥናቱ ተሳታፊዎች ከ1 እስከ 40 ቁጥር እንዲጠሩና በሳምንቱ መጨረሻ ያከናወኑትን በአጭሩ እንዲያብራሩ ተደርጓል።

ይህም በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መሳሪያው ውስጥ እንዲገባ ተደርጎ የተሳታፊዎቹ የድምጽ ሞገድ ከጉንፋን ጋር ያለው ዝምድና በጥልቀት ተጠንቷል።

ቀደም ብሎ የጤነኛ ሰዎች ድምጽ ሞገድን ጉንፋን ከያዛቸው እንዲለይ የሰለጠነው ሰው ሰራሽ አስተውሎትም በጥናቱ ከተሳተፉት ውስጥ በትክክልም ጉንፋን የያዛቸውን ለይቷል ተብሏል።
የቴክኖሎጂው ስኬታማነትም የ70 በመቶ ውጤት ተሰጥቶታል ይላል የኢኮኖሚስት ዘገባ።

የሰው ሰራሽ አስተውሎቱ ሰዎች ስልክ በመደወል ብቻ ጉንፋን ይያዝ አያዛቸው ማረጋገጥ የሚያስችል ነው።

ይህም ወደ ህክምና ተቋማት በማምራት የሚባክን ጊዜ እና ገንዘብን ያስቀራል ነው ያሉት ተመራማሪዎቹ።

አንዳንድ ሰዎችም ጉንፋን አሞናል በሚል ከስራ ለመውጣት የሚያደርጉትን ጥረት ከንቱ ያደርግባቸዋል፤ በቢሮ ውስጥ ቴክኖሎጂውን በመጠቀም በርግጥም በጉንፋን መያዝ አለመያዛቸውን ማረጋገጥ ስለሚቻል።

የህንድ ተመራማሪዎች ይፋ ያደረጉት ቴክኖሎጂ የሰው ሰራሽ አስተውሎት በጤናው ዘርፍ እያበረከተ ያለው ጉልህ አስተዋጽኦ ማሳያ ተደርጎ ቀርቧል።

23/12/2023

የምናስነጥሰው ለምንድን ነው? ንጥሻን ለማስቆም መሞከርስ ምን ጉዳት አለው?
በስኮትላንድ አፍና አፍንጫውን በማፈን ላለማስነጠስ የሞከረው ግለሰብ ከባድ ጉዳት ደርሶበታል
የህክምና ባለሙያዎች ንጥሻን መከላከል በጆሮ ታምቡርና በጉሮሮ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያስከትል አሳስበዋል

ንጥሻ ወደ መተንፈሻ አካላት የሚገባ ጎጂ ነገርን ለመከላከል ሰውነታችን በተፈጥሮው የሚሰጠው ምላሽ ነው።

ስናስነጥስ አፍና አፍንጫችን በክርናችን ወይም በእጃችን መሸፈንና እጃችን መታጠብም የተላላፊ ቫይረሶችን ስርጭት ለመቀነስ እንደሚያግዝ የህክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ።

ይህን ተፈጥሯዊ ሂደት ማስቆምም ከባድ የጤና ችግር እንደሚያስከትል ይገልጻሉ።

በስኮትላንድ ዱንዴ በተባለ አካባቢ ንጥሻን ለማስቆም የሞከረ ግለሰብ ራሱን ስቶ ሆስፒታል መግባቱም የጉዳዩን አሳሳቢነት አሳይቷል።

ስሙ ያልተጠቀሰውና በ30ዎቹ የእድሜ ክልል የሚገኘው ግለሰብ አፉንና አፍንቻውን ዘግቶ ንጥሻውን ለማስቆም በመሞከሩ ነው በጉሮሮው ላይ ጉዳት የደረሰበት።

በከተማዋ የኒንዌልስ ሆስፒታል የህክምና ባለሙያዎች እንደሚሉት፥ ንጥሻን ለማስቆም አፍና አፍንጫን በተመሳሳይ ማፈን በላይኛው የመተንፈሻ አካል ላይ የሚፈጠር ግፊትን በ20 እጥፍ ይጨምራል።

ይህም በጆሮ ታምቡር፣ በጉሮሮ እና ከበድ ሲልም በአይንና በጆሮ የደም ቱቦዎች ላይ ጉዳት እንደሚያደርስ ነው የተናገሩት።

መኪና እያሽከረከረ እያለ ንጥሻን ለማቆም የሞከረው ወጣት ምርመራ ሲደረግለት በጉሮሮው ላይ 2 ሚሊሜትር የሚረዝም ክፍተት መገኘቱ ተገልጿል።

ግለሰቡ ቀዶ ህክምና ባያስፈልገውም ለቀናት ህክምናውን ተከታትሎ ከሆስፒታል ወጥቷል፤ ለሁለት ሳምንትም ከባድ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እንዳያደርግ ታዟል።

እምብዛም የማይከሰተው አደጋ በስኮትላንዳዊው ወጣት ታይቷል የሚሉት ዶክተር ራሳድ ሚሲሮቭስ፥ ከግለሰቡ ድርጊት መማር እንደሚገባ ያሳስባሉ።

“እንደ ሳይነስ እና አለርጂ ያሉ ችግሮች ንጥሻን ቢያበዙና ሰዎችን ቢያማርሩም ንጥሻን ለማስቆም መሞከር ግን አደገኛ ነው” የሚሉት ዶክተር ሚሲሮቭስ፥ ንጥሻን ማስቆም ሳይሆን በዚሁ ጊዜ የሚወጣን ቫይረስ ወደሌሎች እንዳይሰራጭ በእጅና ክርን መሸፈኑ ሁሌም ሊዘነጋ አይገባም ብለዋል።

በ2018 በሌስተር መሰል ሙከራ ያደረገ ግለሰብ ጉሮሮው ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት ቢቢሲ በዘገባው አስታውሷል።

የአልኮል ሱሰኝነትን ለመቆጣጠር ኬንያ የመጠጥ ቤቶችን ቁጥር ልትወስን ነው ******************ምንጭ ቢቢሲኬንያ የአልኮል አዘውታሪነትን ለመቆጣጠር በሚል በግዛቶቿ በሚገኙ ከተሞች ውስ...
29/01/2023

የአልኮል ሱሰኝነትን ለመቆጣጠር ኬንያ የመጠጥ ቤቶችን ቁጥር ልትወስን ነው
******************
ምንጭ ቢቢሲ
ኬንያ የአልኮል አዘውታሪነትን ለመቆጣጠር በሚል በግዛቶቿ በሚገኙ ከተሞች ውስጥ አልኮል የሚሸጡ መጠጥ ቤቶች ቁጥር ውስን እንዲሆን የወጣው ትዕዛዝ ተግባራዊ እንዲሆን አዘዘች።
የአገሪቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ሪጋቲ ጋቻግዋ በአገሪቱ ማዕከላዊ ክፍል ውስጥ የሚገኙ የመንግሥት መስተዳደሮች ባለፈው ሳምንት ይፋ የሆነውን “በአንድ ከተማ አንድ መጠጥ ቤት” የሚለውን መመሪያ ተግባራዊ እንዲያደርጉ አዘዋል።
በተጨማሪም የአልኮል ሱሰኝነትን ለመቆጣጠር ምክትል ፕሬዝዳንቱ የመዝናኛ ስፍራዎች ክፍት መሆን ያለባቸው ከአመሻሽ 11 ሰዓት አስከ ምሽት አምስት ሰዓት ብቻ እንዲሆን አዘዋል።
ነገር ግን ይህ የኬንያ መንግሥት ትዕዛዝ በርካቶች የተለያዩ ጎጂ ኬሚካሎች ወደ ሚጨመሩባቸው እና በቤት ውስጥ ወደ ሚጠመቁ መጠጦች ፊታቸውን ሊያዞሩ ይችላሉ የሚል ስጋት ፈጥሯል።
ምክትል ፕሬዝዳንቱ ግን በአሁኑ ወቅት በተለይ በማዕከላዊው የኬንያ ግዛቶች ውስጥ የአልኮል ሱሰኝነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ እርምጃ እንዲወሰድ አዘዋል።
“ይህንን ችግር በመጋፈጥ ቀጣዩን ትውልድ እንታደግ፣ ይህንን ካላደረግን ግን እንደ ማኅበረሰብ ችግር አለብን ማለት ነው” ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ከአስተዳዳሪዎች ጋር ባደረጉት ስብሰባ ላይ ተናግረዋል።
በተጨማሪም ሪጋቲ ጋቻግዋ የግዛት አስተዳደሮች መጠጥ ቤቶች ማውንት ኬንያ በሚባለው አካባቢ ለበርካታ ወጣቶች በዕጽ እና በአልኮል ሰበብ መጥፋት ምክንያት በመሆናቸው የተሰጣቸው የሥራ ፈቃድ ጊዜ ሲያበቃ እንዳይታደስላቸው አዘዋል።
ምክትል ፕሬዝዳንቱ የወጣቱን ትውልድ ሕይወት እያበላሹ ነው ሲሉ የከሰሷቸው መጠጥ ቤቶች ብዛት በአካባቢው ካሉ ሱቆች በላይ መሆኑን በመግለጽ እርምጃው በአስቸኳይ ተግባራዊ እንዲሆን አዘዋል።
ፖሊስ እና የግዛት አስተዳዳሪዎች የትኛውም የመዝናኛ ቦታ 24 ሰዓት እንዳይሰራ እንዲከለክሉ ያዘዙት ምክትል ፕሬዝዳንት ጋቻግዋ “ትውልድ እንዲጠፋ ከፈቀድን እንጸጸታለን፤ ስለዚህ አሁኑኑ እርምጃ እንውሰድ” ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
የአልኮል ሱሰኝነት በኬንያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ከመሆኑ በተጨማሪ በርካታ ወጣቶችን በመሳብ ለጉዳት እያደረገ በመሆኑ ነው መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ እርምጃ መውሰድ እንዲጀምር የተገደደው።

These 6 Types of Music Are Known to Dramatically Improve ProductivityMusic isn't just a means of entertaining ourselves:...
28/01/2023

These 6 Types of Music Are Known
to Dramatically Improve Productivity
Music isn't just a means of entertaining ourselves: it can also encourage creativity and help us become more productive. Listening to music can also be therapeutic, relieving feelings of stress so you can concentrate better.
Research has found that certain types of music can be beneficial to us while we work. Some types of music seem to help with learning and improve our ability to process information. Other types help block out distracting background noise. Still other types sync with our brain waves to induce "eureka moments."
So, if you're struggling with productivity and want to know what you should be listening to, read on. These are the six types of music that will give you a major boost in productivity.
1. Classical Music
Researchers have long claimed that listening to classical music can help people perform tasks more efficiently. This theory, which has been dubbed "the Mozart Effect," suggests that listening to classical composers can enhance brain activity and act as a catalyst for improving health and well-being. Various studies have confirmed that listening to classical music enhances one's ability to manipulate shapes and solve spatial puzzles.
The absence of words in the music may be one factor, as songs that contain lyrics have been found to be a distraction when you're trying to focus. And classical music is known for being calming, relaxing and helping reduce stress. This genre of music has been found to help students perform 12 percent better on their exams. Some selections, like Beethoven's "Für Elise," seem to help students study longer and retain more information.
2. Nature Music
Listening to the sounds of nature, like waves crashing or a babbling brook, has been shown to enhance cognitive function and concentration. Nature sounds work best when they're soothing sounds, such as flowing water or rainfall, while more jarring noises such as bird calls and animal noises can be distracting.
Researchers at Rensselaer Polytechnic Institute have discovered that natural sounds boost moods and focus. The study found employees were more productive and had more positive feelings when nature sounds were playing in the background while they worked.
This may be because nature sounds helped mask harsher, more distracting noises, such as people talking or typing. Researchers found that workers not only performed better on tasks, but calming nature sounds also had a restorative effect on cognitive abilities.
3. Cinematic Music
An intense film score can make you feel like you're doing something inspiring or important, even if you're just chipping away at your to-do list. A grandiose, epic soundtrack playing in the background may make even the most mundane tasks feel like you're changing the world, thus heightening your concentration and productivity.
Cinematic music scores can be empowering, lifting your spirits and brightening your mood. So, if you're feeling tired and drained, try listening to some epic-style cinematic music to give you that extra boost of motivation.
4. Video Game Music
It might seem strange, but listening to music composed for video games can be a great tool to help you focus. Every element of a video game is designed to create an enhanced gaming experience for all your senses, and the music has been composed specifically to help you focus on your task without being distracted by a cacophony of sounds.
This music generally has no lyrics or human voices and is fairly fast-paced to keep you moving forward. Many of these video games involve solving puzzles and dealing with intense situations, so you're subjecting yourself to simulated stressful challenges. Video games have invested a lot of resources in figuring out the perfect balance to the music they use.
Video game music is composed in a way that keeps you engaged as you evaluate, navigate and often fight your way through these make-believe worlds. These musical compositions may be just the thing to propel you onward and keep you zooming through your tasks and daily to-do list.
5. Music between 50 and 80 beats per minute
Some research suggests that it's not the type of music that's important in helping you stay focused and productive, but the tempo of that music. Studies have found that music with 50 to 80 beats per minute can enhance and stimulate creativity and learning.
Dr. Emma Gray, a cognitive behavioral therapist, worked with Spotify to research the benefits of certain types of music. She found that listening to music set in the 50- to 80-beat range puts the brain into an alpha state.
When we're awake, we're typically in a state of mind known as beta, a heightened state of alertness where our brain-wave activity is between 14 and 30 HZ. When our brain slows to between 7 and 14 HZ, we're in a more relaxed alpha state of mind that allows us to be more receptive and open, and less critical. This state of mind is what scientists associate with activities that involve our imagination, memory and intuition, including our "eureka moments."
If you have ever listened to music that you're familiar with, only to find yourself deep in thought and not really hearing the music at all, this is an alpha state induced by music. You're tuning out while being tuned in.
It works best to find songs you're familiar with and set at 50 to 80 beats per minute. Here's a playlist of songs in that range, including these popular tunes:
6. Your favorite music
When it comes to tackling projects that you're not really excited about, it can help to put on music you enjoy. Studies have found that putting on your favorite type of music can improve your mood and productivity.
Teresa Lesiuk, an assistant professor in the music therapy program at the University of Miami, found that personal choice in music is important when deciding what to listen to while working, especially for those who are moderately skilled at their jobs. Her research found that participants who listened to music they enjoyed completed their tasks faster and came up with better ideas than those who didn't because the music helped them feel better and improved their mood.
The only time this didn't hold true was if the music participants listened to was distracting, such as having a beat that was too fast or lyrics that caught their attention.

28/01/2023

ረጅምና ጤናማ እድሜ ለመኖር የሚጠቅሙ የምግብ አይነቶች በጥቂቱ:-
ዶ/ር ሆሊያት
*አትክልትና ፍራፍሬዎች
• በውስጣቸው የሚይዙት የካሎሪ መጠን አነስተኛ ስለሆነና በፋይበርና የተለያዩ ንጥረነገሮች የተሞሉ ስለሆኑ ለጤና ተመራጭ ናቸው።
*ጨው በአነስተኛ መጠን መመገብ
• የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ አነስተኛ የጨው መጠንን መመገብ ለደም ግፊት ያለንን ተጋላጨነት ይቀንሳል። ይህም በተዘዋዋሪ የአንጎል ሴሎች እንዳይጎዱ በማድረግ ከእድሜ መጨመር ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮች እንዳይከሰቱ ያግዛል።
*በካልሲየም የበለፀጉ ምግቦች
• የአጥንት መሳሳት ከእድሜ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ቢሆንም በተቻለ መጠን ጉዳቱን ለመከላከል በከልሲየም የበለፀጉ ምግቦችን ማዘውተር ጠቀሜታ አለው።
*ቡና
• በአብዛኛው የተደረጉ ጥናቶች ስንመለከት ቡና ያልተጠበቁ የጤና ጥቅሞች አሉት። ለስኳር ህመም ተጋላጭነትን ከመቀነስ ባለፈ ቡናን ሳይበዛ መጠጣት ከእድሜ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮች እንዳይከሰቱ ያደርጋል።
*ቲማቲም
• ቲማቲም በፋይበር እና በቫይታሚኖች የበለፀጉ ስለሆነ እና ካንሰርን የመከላከል አቅም ስላለው ለጤናማ እና ረጅም እድሜ ተመራጭ ያደርገዋል።
*ሶያ
• ከፍተኛ የሆነ የፕሮቲን ምንጭ የሆነው ሶያ ስጋን እና ሌሎች የፕሮቲን ምንጮችን የሚተካ በተፈጥሮ አትክልት የሆነ ምግብም ነው።
የነጭ ሽንኩርት የጤና ጥቅሞች
• በነጭ ሽንኩርት ውስጥ የሚገኝ ንጥረ ነገር በፈንገስ ምክንያት ለሚከሰቱ የቆዳ ሕመሞች መድኃኒትነት አለው፡፡
• በከፍተኛን ደረጃ ባክቴሪያንና ቫይረሶችን የማጥፋት ብቃት ያለው የምግብ ዓይነት ነው፡፡
• ነጭ ሽንኩርት በውስጡ የደም መርጋትን የሚከላከል ንጥረ ነገርን ይይዛል፡፡
• የደም ግፊት መጨመርን ይከላከላል፡፡
• ከዕድሜ መጨመር የተነሳ የሚከሰት የደም ቧንቧ ጥበትን የመከላከል ጥቅም ያለው ነጭ ሽንኩርት ይህንን በማድረግ በደም ቧንቧ ጥበት ምክንያት የሚከሰት የልብ ሕመምን ይከላከላል፡፡
• በሰውነታችን ውስጥ ያለውን የኮሌስትሮል መጠን በመቀነስ በደም ቧንቧ ላይ የሚገኘውን የስብ መጠን እንዲቀንስ ያድርጋል፡፡
• ሰውነታችን በአለርጂ እንዳይጠቃ የማድረግ አቅምም አለው፡፡ በሰውነት ላይ ለሚወጣ ሽፍታና በአንዳንድ ነፍሳት ምክንያት የሚወጣንን ሽፍታም ይከላከላል፡፡
• ነጭ ሽንኩርት በጉንፋን የመያዝ ሁኔታን በከፍተኛ ደረጃም ይቀንሳል፡፡ከተያዝንም በኋላ እንዳይበረታብንና ቶሎም እንድንድን ይረዳል፡፡
• ነጭ ሽንኩርት በሰውነታችን የሚመነጨውን የኢንሱሊን መጠን መጨመርና በደም ውስጥ የሚገኙትን የስኳር መጠን በመቆጣጠር ለስኳር ሕመም ጠቀሜታነት ይሰጣል፡፡
• የተፈጨ ነጭ ሽንኩርት ጥርሳችንን በሚያመን ቦታ ላይ በማድረግ ባክቴሪያዎችን ማጥፋትና ሕመምን የመቀነስ ጥቀም አለው፡፡

28/01/2023

ረጅም ዕድሜ የመኖር ሚስጥር በኦኪናዋ ተገኝቶ ይሆን?
ጃፓን የሚገኘው የንቁ! ዘጋቢ እንደጻፈው
• በጃፓን ባሉት የኦኪናዋ ደሴቶች ውስጥ በ2006 ከነበረው 1.3 ሚሊዮን ሕዝብ መካከል 740 የሚያህሉት ዕድሜያቸው 100 ዓመትና ከዚያ በላይ እንደሚሆናቸው ተገምቷል፤ ከእነዚህም ውስጥ 90 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው።
• በኦኪናዋ ዕድሜያቸው 100 ዓመትና ከዚያ በላይ በሆናቸው ሰዎች ላይ የተደረገውን ጥናት የመሩት ዶክተር ማኮቶ ሱዙኪ እንደገለጹት ከ100,000 ሕዝብ መካከል 50 የሚያህሉት ዕድሜያቸው 100 እና ከዚያ በላይ ነው። በአብዛኞቹ የበለጸጉ አገሮች ውስጥ በዚህ ዕድሜ ላይ የሚገኙ አረጋውያን ብዛት ከ100,000 ሕዝብ መካከል ከ10 እስከ 20 እንደሚሆን ይገመታል።
• “ዕድሜያቸው 100 ዓመትና ከዚያም በላይ በሆኑ ሰዎች ላይ ከሚደረጉት ጥናቶች መካከል ባስቆጠረው ጊዜ በዓለም ላይ ተወዳዳሪ ያልተገኘለት” እንደሆነ የሚነገርለት አንድ ጥናት እንዳመለከተው “ከሚጠበቀው በላይ በርካታ የሆኑ በዚህ ዕድሜ ላይ የሚገኙ አረጋውያን እጅግ ጤነኞች [ነበሩ።]” ይህ የሆነበትን ምክንያት ለመረዳት ሱዙኪና ቡድናቸው በዚህ ዕድሜ ላይ በሚገኙ ከ900 በሚበልጡ አረጋውያን እንዲሁም በ70ዎቹ ወይም ከዚያ በላይ ዕድሜ ባላቸው የኦኪናዋ ሰዎች የአኗኗር ዘይቤና የጂን አወቃቀር ላይ ምርምር አካሄዱ። ጥናት የተካሄደባቸው አረጋውያን በአመዛኙ ቀጠን ያሉና ጤነኞች እንደሆኑ፣ የደም ሥራቸው ከኮሌስትሮል የጸዳ እንደሆነ፣ የሚገርመው ደግሞ በካንሰርና በልብ በሽታ የመጠቃት አጋጣሚያቸው ዝቅተኛ እንደሆነ ተመራማሪዎቹ ደርሰውበታል። እንዲሁም በኦኪናዋ የሚኖሩት በ90ዎቹ መገባደጃ ላይ የሚገኙ አረጋውያን ለአእምሮ በሽታ የመጋለጣቸው አጋጣሚ በሌሎች የበለጸጉ አገሮች ከሚገኙት የዕድሜ እኩዮቻቸው ጋር ሲነጻጸር በጣም አነስተኛ ነው። ሚስጥሩ ምን ይሆን?
• በዋነኝነት የሚጠቀሰው የጂናቸው ባሕርይ ነው። ይሁን እንጂ ሌሎች ምክንያቶችም አሉ። ከእነዚህም ውስጥ ከትንባሆ መራቅ፣ በአልኮል መጠጥ አወሳሰድ ረገድ ልከኛ መሆንና ጥሩ አመጋገብ ይገኙበታል። ኦኪናዋውያን አነስተኛ የካሎሪ መጠን ያለው ምግብ የሚመገቡ ከመሆኑም በላይ አትክልት፣ ፍራፍሬ፣ በአሰር የበለፀጉ ምግቦችና አነስተኛ የኮሌስትሮል መጠን ያላቸው የቅባት ምግቦች ያዘወትራሉ። ከዚህም በላይ ሕዝቡ እስኪጠግብ ደረስ የመብላት ልማድ የለውም። በጥናቱ ውስጥ የተካፈሉት ዶክተር ብራድሌይ ዊልኮክስ “ትንሽ የመጥገብ ስሜት ሲሰማህ መብላትህን ማቆም አለብህ” በማለት ይናገራሉ። “ሆድህ እንደሞላ ለአእምሮህ መልእክት የሚልከው ከ20 ደቂቃ በኋላ ነው።”
• ኦኪናዋውያን የሚቀመጡበት ጊዜ የላቸውም ለማለት ይቻላል፤ አትክልት ይንከባከባሉ፣ በየቀኑ በእግር ይሄዳሉ፣ ባሕላዊ ጭፈራ ይጨፍራሉ ወይም በሌሎች እንቅስቃሴዎች ይካፈላሉ። ዕድሜያቸው 100 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸው አረጋውያን ባሕርያቸው ሲጠና ብሩሕ አመለካከት ያላቸውና ከሁኔታዎች ጋር በቀላሉ የሚላመዱ እንደሆኑ ተደርሶበታል። ውጥረትን በጥሩ ሁኔታ የሚቋቋሙ እንደሆኑና በተለይም ሴቶቹ “ጠንካራ ማኅበራዊ ትስስር” እንዳላቸው ታይቷል።
• ረዥም ዕድሜ ለመኖር የሚረዳ “ተአምራዊ መድኃኒት የለም” በማለት ዊልኮክስ ይናገራሉ። ረዥም ዕድሜ መኖር በዘር ውርስ፣ በጥሩ አመጋገብ፣ በአካላዊ እንቅስቃሴ፣ በጥሩ ልማዶች፣ “እንዲሁም ውጥረትን በተሳካ መንገድ በመቋቋም ችሎታ” ላይ የተመካ እንደሆነ ጥናቱ አመልክቷል።

አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ ***************** በፊልም ሥራዎቹ ብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነትን እና ዝናን ያተረፈው አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ከዚህ ዓለ...
11/12/2022

አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
*****************
በፊልም ሥራዎቹ ብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነትን እና ዝናን ያተረፈው አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ (ባባ) ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።
ወጣቱ የፊልም ባለሙያ ባደረበት ሕመም ለሳምንታት በሕክምና ሲረዳ ቢቆይም ሕይወቱ ሊያልፍ ችሏል።
አርባ ያህል ፊልሞች ላይ የተወነው አርቲስት ታሪኩ በሕመም ምክንያት ሕይወቱ ማለፉን ኢፕድ ከአርቲስቱ የቅርብ ሰዎች ማረጋገጡን ዘግቧል።
አርቲስቱ ወጣት በ97፣ ወንድሜ ያዕቆብ፣ ላውንድሪ ቦይ፣ ማርትሬዛ፣ ይመችሽ-የአራዳ ልጅ 2፣ ሞኙ የአራዳ ልጅ 4፣ አንድ ሁለት፣ ብር ርርር፣ ወደው አይሰርቁ፣ ወፌ ቆመች፣ እንደ ቀልድ፣ ወቶ አደር፣ አባት ሀገር እና ሌሎችም ፊልሞች ላይ ተውኗል።
አርቲስት ታሪኩ ብርሃኑ የአንድ ልጅ አባት ነበረ።

ራስ ምታትራስ ምታት በሁሉም ፆታ እና እድሜ ላይ ሊያጋጥም የሚችል እና ብዙዎቻችንን የሚያጠቃ ህመም አይነት ነው፡፡ራስ ምታት በምን ምክንያት ይከሰታል?ራስ ምታት በተለያዩ ምክንያቶች ሊከሰት ...
04/12/2022

ራስ ምታት
ራስ ምታት በሁሉም ፆታ እና እድሜ ላይ ሊያጋጥም የሚችል እና ብዙዎቻችንን የሚያጠቃ ህመም አይነት ነው፡፡
ራስ ምታት በምን ምክንያት ይከሰታል?
ራስ ምታት በተለያዩ ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል፡፡ የራስ ምታታችንን ምክንያት ስናውቀው ለመታከም እና ለመዳን ቀላል ይሆንልናል፡፡
1.ፕራይመሪ (የመጀመሪያ ደረጃ) የራስ ምታት፡- እንደ ማይግሬን ያሉ የራስ ምታቶች በጭንቅላታችን ውስጥ ባሉ የደም ቧንቧዎች፤ ነርቮች እና ጡንቻዎች ላይ በሚፈጠር ጫና ምክንያት የሚመጡ ናቸው፡፡ ወይንም ደግሞ በአእምሮዋችን ውስጥ ባለው የኬሚካል መቀያየር የሚመጡ ናቸው፡፡
2.ሰከንደሪ (ሁለተኛ ደረጃ) የራስ ምታት፡- ራስ ምታት የሌላ በሽታ ምልክት ሲሆን ሰከንደሪ ራስ ምታት ይባላል፡፡ ለምሳሌ ጉንፋን ሲይዘን፤ ታይፈስ ታይፎይድ ስንታመም፤ በደም ግፊት ምክንያት፤ መጠጥ አብዝተን ስንጠጣ፤ ሳይነሳችን ሲነሳብን፤ እና በመሳሰሉት ምክንያት ራሳችንን ያመናል፡፡ ይሄ አይነት ራስ ምታት ነው ሁለተኛ ደረጃ ራስ ምታት የሚባለው፡፡
መቼ ነው ወደ ሃኪም መሄድ ያለብን?
ራስ ምታት በማስታገሻ መድሃኒቶች ስለሚታገስ ማስታገሻ በመውሰድ ልንድን እንችላለን፡፡ ነገር ግን ራስ ምታታችን
• የሚደጋገም ከሆነ
• በሳምንት ከሁለት ጊዜ በላይ በራስ ምታት ምክንያት የማስታገሻ መድሃኒት የምንወስድ ከሆነ
• እየተደጋገመ የሚያመን ከሆነ እና ህመሙ እየጨመረ ከመጣ
• የጀመረን ራሳችንን ከተጋጨን ወይም አደጋ ከደረሰብን በኋላ ከሆነ
• ስራችንን በራስ ምታት ምክንያት መስራት የሚያቅተን ከሆነ
• በማስታገሻ መድኃኒት አልድንም ካለ
ከራስ ምታት ጋር አብሮ ግራ መጋባት፤ ማቅለሽለሽ፤ ማስመለስ፤ ድንዝዝ ማለት፤ የአንገት ህመም፤ ማዞር፤ የጆሮ ወይም የአፍንጫ ህመም፤ ራስን መሳት፤ እይታ መከልከል፤ ድካም እና የመሳሰሉት ምልክቶች ካሉ ወደ ሃኪም ቤት አንድንሄድ ይመከራል፡፡
ራሳችንን ሲያመን በቤት ውስጥ ምን ማድረግ አንችላለን?
ብዙዎቹ መድሃኒቶች የራሳቸው የሆነ የጎንዮሽ ጉዳት ይኖራቸዋል፡፡ ለምሳሌ የህመም ማስታገሻዎችን መውሰድ ካበዛን የጨጓራ ቁስለት ወይም የኩላሊት ችግሮችን ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ ቶሎ መድሃኒት ከመውሰድ በቤት ውስጥ ተፈሯዊ የሆኑ መፍትሄዎችን መጀመሪያ ብንሞክር ይሻላል፡፡ ካልሆነ ግን ማስታገሻ መድኃኒት መውሰድ ነው፡፡
1. ውሃ መጠጣት፡- በሰውነታችን ውስጥ ያለው ውሃ ሲቀንስ የራስ ምታት ይነሳል፡፡ ስለዚህ ውሃ መጠጣት መፍትሄ ሊሆን ይችላል ማለት ነው፡፡ ከውሃ እጥረት የተነሳ ከሆነ ራሳችንን ያመመን ቶሎ ውሃ መጠጣት ያለብን ሲሆን ህመሙም ከሰላሳ ደቂቃ እሰከ ሶስት ሰአት ድረስ ባለው ጊዜ ይለቀናል፡፡
2. ቀዝቃዛ ወይም ሙቅ ነገር ጭንቅላታችን ላይ ማድረግ፡- ይሄ መፍትሄ ከሰው ሰው ይለያያል፡፡ አንዳንድ ሰዎች በረዶ ወይም በቀዝቃዛ ውሃ ውስጥ የተነከረ ጨርቅ ጭንቅላታቸው ላይ ማድረግ ራስ ምታትን ያስታግስላቸዋል፡፡ አንዳንድ ሰዎች ደግሞ ሙቅ ሻወር መውሰድ ወይም በሙቅ ውሃ ውስጥ የተነከረ ጨርቅ ጭንቅላታቸው ላይ ማድረግ ራስ ምታት ያስታግስላቸዋል፡፡
3. በማግኒዚየም የበለፀገ ምግብ መመገብ፡- ማግኒዚየም ለጤናችን በጣም ጠቃሚ የሆነ ንጥረ ነገር ሲሆን በሰውነታችን ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን እንዲሁም ነርቮቻችን የሚያስተላልፉትን መልእክቶች ይቆጣጠራል፡፡ ማግኒዘይም ማይግሬንን ጨምሮ ሌሎችን ራስ ምታቶች ማዳን ይችላል፡፡ ስለዚህ ሃይለኛ ራስ ምታት ካለን ሃኪም አማክረን የምግኒዚየም ክኒኖችን መውሰድ እንችላለን፡፡ ወይም ደግሞ እንደ ሙዝ፤ አቮካዶ፤ አጃ፤ ቡኒ ሩዝ፤ ቦሎቄ፤ ኬል፤ ስፒናች፤ አተር እና ባቄላ የመሳሰሉትን በማግኒዚየም የበለፀጉ ምግቦች በመመገብ በሰውነታችን ውስጥ ያለውን የማግኒዚየም መጠን ማሳደግ እንችላለን፡፡
4. ጠንካራ መአዛ ያላቸውን ነገሮች አለመጠቀም፡- ራስ ምታት ባለባቸው 400 ሰዎች ላይ የተደረገ አንድ ጥናት እንዳሳየው ከሆነ እንደ ሽቶ ወይም ለፅዳት የሚውሉ ኬሚካሎች ያሉ ጠንካራ መአዛዎች ራስ ምታት እንደሚያስነሱ ታይቷል፡፡
5. የዝንጅብል ሻይ መጠጣት፡-ዝንጅብል ሰውነታችን ውስጥ ያሉ አላስፈላጊ ወይም ምርዛማ ንጥረ ነገሮችን ማስወገድ እና ሰውነታችን እንዳይቆጣ ማድረግ ይችላል፡፡ በዛ ላይ ማቅለሽለሽን እና ማስመለሰን ያስታግሳል፡፡ ስለዚህ የዝንጅብል ሻይ መጠጣት የራስ ምታታችንን ሊያስታግሰልን ይችላል፡፡
ለጤና የሚጠቅሙ ፅሁፎችን ለማንበብ ገፃችን ላይክ እነሰ ሼር ያድረጉ፡፡
መልካም ጤንነት

25/11/2022

በሁለት ቀን ሦስት ልጆች

በወለጋ ጠቅላይ ግዛት በጉድሩ አውራጃ በጐበያ ም/ወረዳ ግዛት በግራዝማች አመኑ መልከኝት ውስጥ የምትገኝ የአቶ ደሬሳ ወዬሳ ባለቤት የሆነች እመት አሠጋሽ ምስክር የተባለች በወላድነቷ የታወቀች ሴት መስከረም ፲፫ ቀን ፶፪ ዓ ም አንድ ወንድ ልጅ ከወለደች በኋላ እንደገና በሦስተኛው ቀን ማለት መስከረም ፲፭ ቀን ፶፪ ዓ ም አንድ ወንድ ልጅና አንዲት ሴት ልጅ ወልዳች ። በጠቅላላው ሦስት ልጆች በመውለዷ ሀገሯን የምታኮራ መሆኑ ቢታወቅም ፤ ለጊዜው የሚደርስባትን የዕለት ሁኔታ ሁላችንም ልናውቅላትና ልናዝንላት ይገባናል። ይህንንም ሁኔታ ለማወቅ የቻልነው የክፍሉ ወረዳ ዋና ጸሐፊ አቶ ጳውሎስ ለአውራጃው ገዥ ለተከበሩ ደጃዝማች ተስፋዬ ወልዴ በቁጥር ፩፻፴፩/፴፮ መስከረም ፳፯ ቀን ፶፪ ዓ ም ሲጽፉ ባደረጉልን ግልባጭ ስለሆነ፤ የነገሩ እርግጠኝነት የሚታመን ነው።

የሕፃናቱ ማደግ ያለማደግ የሚታወቀው የፈጠራቸው ብቻ መሆኑን ከተገነዘብን በኋላ፤ ፅንሳቸው ወይም ዘራቸው እንዴት ነው? የማለት ሀሳብ ይታገለን ይሆናል።

የወለጋ ጠቅላይ ግዛት አዣንስ ኃይለመስቀል ወልደየስ

(በኅዳር 29 ቀን 19 52

ከወጣው አዲስ ዘመን ጋዜጣ)

የአዲሱ የውሀ መዋኛ መመረቅመስከረም ፳፱ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ. ም ከዕኩለ ቀን በላይ በ፱ ሰዓት በግዮን ሆቴል ቅጽር ግቢ ውስጥ አዲስ የተሠራ የውሀ መዋኛ ሥፍራ በልዑል ሣህለ ሥላሴ ኃይለሥላሴ ...
25/11/2022

የአዲሱ የውሀ መዋኛ መመረቅ
መስከረም ፳፱ ቀን ፲፱፻፶፪ ዓ. ም ከዕኩለ ቀን በላይ በ፱ ሰዓት በግዮን ሆቴል ቅጽር ግቢ ውስጥ አዲስ የተሠራ የውሀ መዋኛ ሥፍራ በልዑል ሣህለ ሥላሴ ኃይለሥላሴ የገሙ ጎፋ ጠቅላይ ግዛት አስተዳዳሪ ተመርቆ ተከፍቷል።
በአመራረቁ ሥነ ሥርዓት ላይ ንጉሣውያን ቤተ ሰብ፤ ክቡራን ሚኒስትሮችና መኳንንት፤ እንዲሁም የውጭ ሀገር መንግሥታት እንደራሴዎች ተገኝተው ነበር።
የአዲሱ መዋኛ አካባቢ በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማና በልዩ ልዩ ኅብረ ቀለማት ባላቸው ጌጣ ጌጦች አምሮና አሸብርቆ ከመገኘቱም በላይ፤ በብዙ መቶ የሚቆጠር ሕዝብ ወደ በዓሉ ሥፍራ ሔዶ የአመራረቁን ሥነ ሥርዓት ተመልክቷል።
ልክ ፱ ሰዓት ሲሆን፤ ልዑል ሣህለ ሥላሴ ደርሰው በተዘጋጀላቸው ሥፍራ ላይ እንደተቀመጡ ስድስት ዋናተኞች ከአምስት ሜትር ርቀት ላይ እየዘለሉ ወደ ተከተረው ውሀ በመጥለቅ፤ የአጠላለቅ ዋና አሳዩ።
(ጥቅምት1 ቀን 1952
ከወጣው አዲስ ዘመን)

የቶኪዮ ነዋሪዎች ኃይል ለመቆጠብ ሲባል ‘አንገተ ሙሉ’ ሹራብ እንዲለብሱ ተጠየቁ**********************ምንጭ፡- ቢቢስየቶኪዮ አገረ ገዢ ዩሪኮ ኮይኪ፣ በመጪው የአገሪቱ የክረምት ወ...
19/11/2022

የቶኪዮ ነዋሪዎች ኃይል ለመቆጠብ ሲባል ‘አንገተ ሙሉ’ ሹራብ እንዲለብሱ ተጠየቁ
**********************
ምንጭ፡- ቢቢስ
የቶኪዮ አገረ ገዢ ዩሪኮ ኮይኪ፣ በመጪው የአገሪቱ የክረምት ወቅት የኃይል ፍጆታን ለመቆጠብ ሲባል የከተማዋ ነዋሪዎች ‘አንገተ ሙሉ’ ሹራብ እንዲለብሱ አሳሰቡ።
ሙሉ አንገትን የሚሸፍኑ ሙቀት ሰጪ ልብሶች እየናረ የመጣውን የኃይል አቅርቦት ወጪ ለመቆጠብ እንደሚረዱ ባለሥልጣኗ ገልጸዋል።
የቶኪዮ ከተማ አስተዳደር ሠራተኞች ለነዋሪዎች ትምህርት ምሳሌ ለመሆን አንገተ ሙሉ ሹራቦችን መልበስ ይጀምራሉ።
የኃይል አቅርቦት ወጪ በከፍተኛ ሁኔታ በጨመረባት የጃፓኗ መዲና፣ በመጪው ክረምት ኃይል ለመቆጠብ የተለያዩ እርምጃዎች እየተወሰዱ ይገኛሉ።
የኃይል ፍጆታን እንዴት መቀነስ እንደሚቻል ለነዋሪዎች መመሪያ እየተሰጠም ነው።
ውሳኔውን ለማሳለፍ በተጠራው ስብሰባ የተገኙ አመራሮች አንገተ ሙሉ ሹራብ ለብሰው ታይተዋል።
የቶኪዮ አገረ ገዢ “ነዋሪዎች ከፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በመማር አንተ ሙሉ ሹራብ ይልበሱ” ብለዋል።
ማክሮን አንገት የሚሸፍን ሹራብ በመልበስ ይታወቃሉ። በእርግጥ የፋሽን ምርጫ ይሁን ለኃይል ቁጠባ የተደረገ ግልጽ አይደለም።
“ሙሉ ሹራብ ያሞቃል። ኃይል ይቆጥባል። የካርበን ልቀትንም ይቀንሳል። ይህም በክረምት ወቅት በብልሀት የኃይል ፍጆታ ከምንቆጥብበት መንገድ አንዱ ነው” ብለዋል አገረ ገዢዋ።
ጨምረውም “ስለተፈጠረው የኃይል አቅርቦት መዋዠቅ አዝናለሁ። ግን በመጪው ክረምት እየዘነጥን ስለ ኃይል ቁጠባም ማሰብ አለብን” ሲሉ ተደምጠዋል።
ባለፈው ወር የጃፓን መንግሥት ዜጎች አገልግሎት እየሰጡ ያልሆኑ መብራቶችን እንዲያጠፉ ጠይቀዋል።
ለማሞቂያ ማሽን የሚወጣውን ኃይል ለመቆጠብ ሲባል ቤት ውስጥ ደራርቦ መልበስንም መንግሥት መክሯል።
ፈረንሳይ እና ሌሎችም የአውሮፓ አገራትም ተመሳሳይ ውሳኔ አሳልፈዋል።
ጀርመን የንግድ ተቋማትና ሕንጻዎች አላስፈላጊ መብራት እንዲያጠፉ ወስናለች።
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ወረራ መፈጸሟን ተከትሎ በተቀሰቀሰው ጦርነት ምክንያት በዓለም ዙሪያ የጋዝና የነዳጅ አቅርቦት በመስተጓጎሉ ዋጋቸው ንሯል።
በዚህም ሳቢያ በርካታ የምዕራባውያን አገራት ነዋሪዎች በቀዝቃዛው የክረምት ወራቶቻቸው ወቅት ቤቶቻቸውን እና የሥራ ቦታቸውን ለማሞቅ የሚጠቀሙበትን የኃይል አቅርቦት እንዲቆጥቡ እየተመከሩ ነው።

Address

Addis Abeba
Addis Ababa
51

Telephone

+251989055705

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when GG health & Social Tips posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to GG health & Social Tips:

Share

Category