Z blessed family

Z  blessed family Takeaway service

24/04/2026

26 There is none like unto the God of Jeshurun, who rideth upon the heaven in thy help, and in his excellency on the sky.
Exodus 33:26

15/10/2024

ልብህን ስታስተካክል ቤትህም ይስተካከላል !!
ሰውየው አስር ክፍል ቤት ሠርቶ ብቻውን ሲኖር አንድ
ቀን በሩ ተንኳኳ ሲከፍት ጌታ ነው፡፡ "ውይ አምላኬ ጌታዬ አንተ እኔ ቤቴ መጣህ?" ብሎ በደስታ
ተቀብሎት አንድ ክፍል ቤት ሰጥቶት መኖር ጀመሩ፡፡በሌላ
ጊዜ በሩ ተንኳኳ፣ ሲከፍት ሰይጣን ነው፡፡ተበሳጭቶ ይዘጋና "ጌታዬ ሆይ አንተ እኔ ቤት እያለህ ሰይጣን የእኔን ቤት እንዴት ያንኳኳል?" አለው፡፡ጌታም "ቤቱ የአንተ እንጂ የእኔ አይደለም " አለው፡፡ሰውየውም ተሰምቶት ሁለት
ክፍል ቤት ለጌታ ጨምሮለት እርሱ ሰባት ክፍል ይዞ መኖር ቀጠሉ፡፡ በሩ ተንኳኳ ሲከፈት ሰይጣን ነው።
ተበሳጭቶ ይዘጋና "ጌታዬ ሆይ አንተ እኔ ቤት እያለህ ሰይጣን የእኔን ቤት እንዴት ያንኳኳል? " አለው፡፡ጌታም " ቤቱ የአንተ እንጂ የእኔ አይደለም " አለው፡፡
ሰውየውም ተሰምቶት ከጌታ ጋር እኩል ለእኩል ተካፈለ፡፡ ነገር ግን ቤቱ ከቀድሞ ይልቅ ተንኳኳ ፡፡ አዝኖም
ይዘጋና ጌታ ሆይ አለው፡፡ ጌታም የቀድሞውን መልስ ሰጠው፡፡በዚህ ጊዜ ሰውየው ለራሱ አንድ ክፍል ቤት ይዞ ዘጠኙን ክፍል ቤት ለጌታ ሰጠው፡፡ ነገር ግን
ከቀድሞው ይልቅ በጣም ተንኳኳ፡፡ ቢከፈት ሰይጣን
ነው። በሩን ይዘጋና ወደ ጌታ ሄዶ " ጌታ ሆይ ምሥጢሩ ምንድን ነው? " አለው፡፡ "ጌታ ግን ቤቱ የአንተ እንጂ
የእኔ አይደለም "አለው፡፡በዚህ ጊዜ ዐሥሩንም ክፍል ለጌታ አስረከበ፡፡ ጌታም አንድ ክፍል ቤት ለሰውየው ሰጠው።በሩም ተንኳኳ ጌታም ሊከፍት ተነሣ ሲከፍት ሰይጣን ነው፡፡ሰይጣንም " ይቅርታ የአንተ ቤት መሆኑን አላወቅሁም" ብሎ ሄደ፡፡
ከዚያን ቀን ጀምሮ መንኳኳት ቆመ፡፡ሁሉንም የሕይወታችንን ክፍል ለፈጣሪ ካላስረከብነው መንኳኳት አይቆምም፡፡ 1ዐ% ስንሰጥ ይንኳኳል፡፡ 30% ስንሰጥ ይንኳኳል፡፡ 50% ስንሰጥ ይንኳኳል፡፡ 99% ስንሰጥ ይበልጥ ይንኳኳል፡፡ 1ዐዐ% ስንሰጥ መንኳኳት ይቆማል፡፡ እኛ ከከፈትን ሰይጣን ይገዳደረናል፡፡ ጌታ ሲከፍት ሰይጣን " ይቅርታ የአንተ ቤት መሆኑን አላወቅሁም " ብሎ ይሄዳል፡፡ ጌታ ሰማይን የደስታ አገር ያደረጋት ሙሉ በሙሉ
የፈጣሪ ፈቃድ የጸናባት በመሆኗ ነው፡፡ ባንተም ሕይወት የሰማይ ደስታ የሚመጣው የፈጣሪ ፈቃድ በሕይወትህ ሙሉ በሙሉ ሲፈጸም ነው፡፡ ስለዚህ፡- ፈጣሪን እረኛህ አድርገው፡፡በፍጹም ልብህ ተከተለው፡፡የሚያስፈልጉህ ነገሮችም አንተን ይከተሉሃል፡፡"ሙሉ ሕይወታችንን ለእግዚአብሔር እናስረክብ።"
እግዚአብሔር ማስተዋልን ጥበብን እውቀትን ከፍቅር ጋር እግዚአብሔር ብርሃኔና-መድሃኒቴ ነው።
ይስጠን አሜን!!!!!!!!!!!!

18/09/2023
18/09/2023
21/07/2023
21/07/2023

Address

Addis Ababa

Telephone

+251911772826

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Z blessed family posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share