HARON Coffee House

  • Home
  • HARON Coffee House

HARON Coffee House የጣዕም መጀመሪያ

15/05/2026
  — የጣዕም መጀመሪያ! ☕✨​በስራ ውጥረት ለደከመ አእምሮዎ እረፍት፣ ለቀንዎ ደግሞ አዲስ መነሳሳትን ይፈልጋሉ?​በወልቂጤ ከተማ እውነተኛውን የኢትዮጵያ ቡና ጣዕም በዘመናዊ መስተንግዶ የሚያ...
15/05/2026

— የጣዕም መጀመሪያ! ☕✨

​በስራ ውጥረት ለደከመ አእምሮዎ እረፍት፣ ለቀንዎ ደግሞ አዲስ መነሳሳትን ይፈልጋሉ?

​በወልቂጤ ከተማ እውነተኛውን የኢትዮጵያ ቡና ጣዕም በዘመናዊ መስተንግዶ የሚያገኙበት ብቸኛው ቦታ ።
​✅ ለምን ወደ እኛ ይመጣሉ?
​በጥንቃቄ የተመረጠ ምርጥ የቡና ጣዕም
​ደስ የሚልና ለዓይን የሚማርክ ድባብ፤

​ዛሬውኑ ይጎብኙንና የጥበብ እና የጣዕም ጥምረትን ይለማመዱ!
​📍 አድራሻችን፦ ወልቂጤ መናኸሪያ አካባቢ
📞 ስልክ፦ +251913831724
+251935547123
#​HARON — ለእርስዎ የተመረጠ!

  — የጣዕም መጀመሪያ! ☕✨​በስራ ውጥረት ለደከመ አእምሮዎ እረፍት፣ ለቀንዎ ደግሞ አዲስ መነሳሳትን ይፈልጋሉ?​በወልቂጤ ከተማ እውነተኛውን የኢትዮጵያ ቡና ጣዕም በዘመናዊ መስተንግዶ የሚያ...
13/05/2026

— የጣዕም መጀመሪያ! ☕✨

​በስራ ውጥረት ለደከመ አእምሮዎ እረፍት፣ ለቀንዎ ደግሞ አዲስ መነሳሳትን ይፈልጋሉ?
​በወልቂጤ ከተማ እውነተኛውን የኢትዮጵያ ቡና ጣዕም በዘመናዊ መስተንግዶ የሚያገኙበት ብቸኛው ቦታ ።
​✅ ለምን ወደ እኛ ይመጣሉ?
​በጥንቃቄ የተመረጠ ምርጥ የቡና ጣዕም
​ደስ የሚልና ለዓይን የሚማርክ ድባብ
​ፈጣንና ፕሮፌሽናል መስተንግዶ
​ዛሬውኑ ይጎብኙንና የጥበብ እና የጣዕም ጥምረትን ይለማመዱ!
​📍 አድራሻችን፦ ወልቂጤ መናኸሪያ አካባቢ
📞 ስልክ፦ 0913831724 | 0935547123
#​HARON — ለእርስዎ የተመረጠ!

13/01/2023
25/09/2022

የ 2014/15 አገር አቀፍ የ 12ኛ ክፍል ፈተና ተፈታኞች በመፈተኛ ዩኒቨረስቲዎች ሊኖራቸዉ የሚችሉ መብቶች፡ ግደታዎች፡የተፈቀዱና ያልተፈቀዱ ጉዳዮች
1.የተፈታኞች መብቶች
የተፈታኞች መብት የተፈታኞች መብቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡
• ከፈተና ጥያቄ ውጪ ማንኛውንም ያልተረዳውን ነገር ጠይቆ የመረዳት መብት አለው፡፡
• በየኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ምግብ፣ የህክምና አገልግሎት፣ የማደሪያ ክፍል፣ ፍራሽና ትራስ የማግኘት መብት አለው፡፡
• ማንኛውም ተፈታኝ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ያለውን የቤተ መጽሐፍት፣ የመጸዳጃ ቤቶች፣ የሻወር፣ የካፍቴሪያዎች፣ የሚኒ ሱፐር ማርኬቶች፣ የተለያዩ ሱቆች፣ የመናፈሻና መዝናኛ አገልግሎቶችን የመጠቀም መብት አለው፡፡
• የኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ የጋራ የደህንነት ጥበቃ የማግኘት መብት አለው፡፡
• በፈተና ሰዓት መፈተኛ ክፍል ገብቶ ብርሃናማ የመፈተኛ ቦታ፣ ወንበር፣ መጻፊያ ጠረጴዛ የማግኘት መብት አለው፡፡
• ፈተና ከመጀመሩ አንድ ቀን ቀድሞ ስለፈተናው ገለጻ (ኦሬንቴሽን) የማግኘት መብት አለው፡፡
2. የተፈታኞች ግዴታ
ተፈታኞች የሚከተሉት ግዴታዎች አለባቸው፡፡
• ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከልም ይሁን መፈተኛ ክፍል አድሚሽን ካርድ ይዞ የመገኘት ግዴታ አለበት፡፡
• ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲመጣ የትምህርት ቤት ወይም የነዋሪነት መታወቂያ ይዞ መገኘት አለበት፡፡
• ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ግቢ ከመግባቱ በፊትና ወደ መፈተኛ ክፍል ከመግባቱ በፊት ሙሉ አካላዊ ፍተሻ የመፈተሽ ግዴታ አለበት፡፡
• ማንኛውም ተፈታኝ በዩኒቨርሲቲ ግቢና በመፈተኛ ክፍል የተከለከሉ ቁሳቁሶችን/ዕቃዎችን መያዝ የለበትም፡፡
• ማንኛውም ተፈታኝ እርሳስ፣ ላጲስና የእርሳስ መቅረጫ ይዞ መገኘት አለበት፤
• ማንኛውም ተፈታኝ የፈተና ደንብን የማክበር ግዴታ አለበት፡፡
• ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከል ውስጥና በመፈተኛ ክፍል ውስጥ የፈተና አስፈጻሚዎች የፈተና አስተዳደር ሥራን ውጤታማ ለማድረግና ሁኔታዎችን ለማመቻቸት የሚያደርጉትን ጥረት የመተባበር ግዴታ አለበት፡፡
• ማንኛውም ተፈታኝ ፈተና ከመጀመሩ በፊት መፈተኛ ክፍል የመገኘት ግዴታ አለበት፡፡
• ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን ቡኩሌት ለፈታኙ የማሰረከብ ግዴታ አለበት፡፡
• ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ተመደበበት ዩኒቨርሲቲ ሲመጣ አንሶላ፣ ብርድልብስና የትራስ ጨርቅ ይዞ የመምጣት ግዴታ አለበት።

3. ለተፈታኞች የተፈቀዱ ነገሮች
ተፈታኞች ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲመጡ ይዘው እንዲመጡ እና ግቢ ውስጥ እንዲጠቀሙ የተፈቀዱ ነገሮች የሚከተሉት ናቸው፡፡
 አዲስ ወይም ቀድሞ ለመማርና ለማጥናት ሲጠቀሙበት የነበረ ማስተወሻ ደብተር፣ የትምህርት መጽሐፍ፣ መንፈሳዊ/ኃይማኖታዊ መጽሐፍት፣ ባዶ ወረቀት
 ደረቅ ምግቦች ወይም ሰንባች ምግቦች (ጩኮ፣ በሶ፣ ዳቦ ቆሎ፣ ቆሎ….)
 ገንዘብ (ብር)፣
 የልብስ ወይም የእጅ ቦርሳ፣ የግል ልብስ፣ ጫማ
 የግል ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ (ሳሙና፣ ሞዴስ፣ የጥርስ ብሩሽ፣ የጥርስ ሳሙና፣ የገላ ማድረቂያ ፎጣ፣ ሶፍት፣ ሻምፖ፣ ኮንዲሽነር፣ ሎሽን፣ ቻፕስቲክ፣ የጸጉር ቅባት፣ የፊት ቅባት)
4. ለተፈታኞች የተከለከሉ ነገሮች
 በፈተና ማዕከል (ዩኒቨርሲቲ) እና መፈተኛ ክፍሎች ውስጥ የተከለከሉ ነገሮች የሚከተሉት ናቸው፡፡ ማንኛውንም ዓይነት የጦር መሣሪያ ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡
 ማንኛውንም ዓይነት ስለት እና ሹልነት ያላቸውን ብረታ ብረቶችና ጠንካራ ፕላስትኮች ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡
 ማንኛውም ድምጽ የሚቀዳ፣ ፎቶ የሚያነሳ፣ ቪዲዮ የሚቀርጽ፣ ከቴሌ መስመርም ሆነ ከቴሌ መስመር ውጭ መልዕክት በዲጂታል መንገድ የሚሰጥ ወይም የሚቀበል የግል ዕቃ/መሳሪያ /ቴክኖሎጂ ውጤት፣ ስልክ፣ አይ-ፓድ፣ ታብሌት፣ ኮምፕዩተር፣ ላፕቶፕ፣ ስማርት ሰዓት፣ ማጂክ ብዕር/እስክሪብቶ፣ ማጂክ ኮት/ጃኬት እና ሌሎች ማንኛቸውም ፎቶ፣ ምስል እና ድምጽ የሚቀርጹ የኤሌክትሮኖክስ መሣሪያዎችን በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥም ሆነ ግቢ ዙሪያ ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
 በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ማንኛውንም ዓይነት የግል ፍላሽ ዲስክ፣ ሃርድ ዲስክ፣ ሲዲ፣ ሚሞሪ፣ ሚሞሪ ሪደር፣ ኦ-ቲጂ ኮንቨርተርና መሰል ዕቃዎችን ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
 ማንኛውም አደንዛዥ እጾች (ጫት፣ ሲጋራ፣ በሓኪም ማዘዣ የሌለው መድኃኒት (በሽሮፕም ይሁን በታብሌት፣ ህክምና መስጫ መርፌ)) መያዝ ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
 ማንኛውም ዓይነት የአልኮል መጠጥ ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
 ማንኛውም ዓይነት የአንገት ሐብል፣ የጸጉር ጌጥ፣ የጆሮ ጌጥ፣ የጣት ቀለበት፣ የእጅ አንባር፣ አድርጎ ወይም ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡ (ከልሙጥ የጋብቻ ቀለበት በስተቀረ)
 ፈተና ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በኋላ ወደ ፈተና ክፍል መግባት እና ፈተናው ተጀምሮ 45 ደቂቃ ሳይሞላ ከፈተና ክፍል መውጣት የተከለከለ ነው፡፡
 ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን ቡኩሌት ይዞ መውጣት ተከለከለ ነው፡፡
 በፈተና ሰዓት በመፈተኛ ክፍል ውስጥ ማስቲካ መያዝም ሆነ መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
 በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ በግልም ሆነ በቡድን መጮህ ወይም በጣም ከፍተኛ ድምጽ ማሰማት የተከለከለ ነው፡፡

ትምህርትቤቶች መረጀዉ ለተማሪዎች እንድደርሳቸዉ ማድረግ ይጠበቅባችኃል፡፡

ወደ ቴሌግራም ቻናሌ ይግቡ!
👇👇👇
https://t.me/MuhammedComputerTechnology
https://t.me/MuhammedComputerTechnology
https://t.me/MuhammedComputerTechnology
https://t.me/MuhammedComputerTechnology

20/08/2022

ለእም/አጠ/2ኛ/ደ/ት/ቤት ተማሪዎች በሙሉ የ2015ዓ.ም ምዝገባ የሚጀመረው ከቀን 23/12/2014 ዓ.ም ነው በሚል የተላለፈው መልዕክ መደበኛ የመማር-ማስተማር ስራ የሚጀመረው ከመስከረም 3/1/2016ዓ.ም በመሆኑ ምዝገባው ከቀን 16/12/2014ዓ.ም በሚለው እንዲስተካከል እየገለፅን ተማሪዎች አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ በአካል በመገኘት እንድትመዘገቡ እያሳሰብን በወቅቱ አለመመዝገብ ለተለያዩ ቅጣቶች የሚዳርግ መሆኑን እንገልፃለን ት/ቤቱ

07/08/2022

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከመስከረም 30 ቀን 2015 ጀምሮ እንደሚሰጥ ተገለጸ።

➥የ2014 የትምህርት ዘመን ብሔራዊ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ማጠቃለያ ፈተና ከመስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ፡፡
➵ፈተናው ከመስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚሰጥ የአገልግሎቱ መረጃ ያመላክታል፡፡
ነሐሴ 1/2014

30/06/2022

/ቤት_ማህበረሰብ_በሙሉ

የ2014 ት/ት ዘመን የወላጅ በዓል ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ ልክ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት ላይ ግቢ ተገኝታችሁ የበዓሉ ታዳሚ እንድትሆኑ እናሳስባለን።
ት/ቤቱ

Address

Wolkite

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when HARON Coffee House posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to HARON Coffee House:

  • Want your business to be the top-listed Restaurant?

Share